1 ሳሙኤል 8:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛም እንደ ሌሎቹ ሕዝቦች የሚመራንና ከፊታችን የሚሄድ፥ ጦርነታችንንም የሚዋጋልን ንጉሥ ያለን ሕዝቦች እንሆናለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛም እንደ ሌሎቹ ሕዝቦች የሚመራንና ከፊታችን የሚሄድ፣ ጦርነታችንንም የሚዋጋልን ንጉሥ ያለን ሕዝቦች እንሆናለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ዐይነት ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት እኛን የሚያስተዳድርና ከጠላቶቻችንም ጋር በምንዋጋበት ጊዜ ወደ ጦር ሜዳ የሚመራን ንጉሥ ይኖረናል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛም ደግሞ እንደ አሕዛብ ሁሉ እንሆናለን፤ ንጉሣችንም ይፈርድልናል፤ በፊታችንም ወጥቶ ስለ እኛ ጠላታችንን ይዋጋል” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛም ደግሞ እንደ አሕዛብ ሁሉ እንሆናለን፥ ንጉሣችንም ይፈርድልናል፥ በፊታችንም ወጥቶ ስለ እኛ ይዋጋል አሉት። |
እኔና ሕዝብህ በፊትህ ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል? እኔና ሕዝብህ በምድርም ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ የተለየን የምንሆነው አንተ ከእኛ ጋር በመውጣትህ አይደለምን?”
በተራሮች ራስ ላይ ሆኜ አየዋለሁ፥ በኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ እነሆ፥ ብቻውን የሚቀመጥ ሕዝብ ነው፥ በአሕዛብም መካከል አይቈጠርም።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።
የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ እንደመጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ ግን፥ አምላካችሁ ጌታ ንጉሣችሁ ቢሆንም እንኳን፥ ‘አይሆንም፤ የሚገዛን ንጉሥ እንፈልጋለን’ አላችሁ።
ንጉሥ ሆኖ የሚመራችሁንም ሰው እነሆ፤ አግኝታችኋል። እኔም ዕድሜዬ ገፍቷል፤ ጠጉሬም ሸብቷል፤ ልጆቼም አብረዋችሁ አሉ፤ ከወጣትነት ጊዜዬ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ስመራችሁ ቆይቻለሁ።
እነርሱም፥ “አንተ አርጅተሃል፤ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም፤ ስለዚህ ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሁሉ የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን” አሉት።