Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 6:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ስለዚህም ጌታ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ፤ ርኩስንም አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “ስለዚህ ከመካከላቸው ውጡ፤ ተለዩም፤ ይላል ጌታ። ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ደግሞም ጌታ እንዲህ ብሎአል፦ “ከእነርሱ መካከል ተለይታችሁ ውጡ፤ ርኩስ የሆነውንም ነገር አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ስለ​ዚ​ህም “ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተለ​ይ​ታ​ችሁ ውጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩ​ሳ​ንም አት​ቅ​ረቡ፥ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17-18 ስለዚህም ጌታ፦ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ፦ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 6:17
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እናንተ የጌታን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ፥ እልፍ በሉ፥ ከዚያ ውጡ፥ ርኩስን ነገር አትንኩ፥ ከመካከልዋ ውጡ፥ ንጹሐን ሁኑ።


ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርሷ ዘንድ ውጡ፤


እንግዲህ ወዳጆች ሆይ! ይህ ተስፋ ቃል ስላለን፥ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፥ እግዚአብሔርን በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርግ።


ስለዚህ ለአባቶቻችሁ አምላክ ለጌታ ተናዘዙ፥ ፈቃዱንም አድርጉ፤ እራሳችሁንም ከምድሪቱ ሕዝቦችና ከእንግዶች ሴቶች ለዩ።”


እርሱም ለማኅበሩ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “እባካችሁ፥ ከእነዚህ ክፉዎች ድንኳን ርቃችሁ ገለል በሉ፤ በኃጢአታቸውም ሁሉ እንዳትጠፉ የእነርሱ የሆነውን ሁሉ አትንኩ።”


አላዋቂነትን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በማስተዋልም መንገድ ሂዱ።”


በብዙ ሌላ ቃልም መሰከረና “ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ፤” ብሎ መከራቸው።


ከባቢሎን ውስጥ ሽሹ፥ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፥ የጌታ የበቀል ጊዜ በእርሷ ላይ ነውና፥ እርሱም ብድራትዋን ይከፍላታልና።


ከምርኮ የተመለሱት የእስራኤል ልጆች፥ የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመፈለግ ራሳቸውን ከምድር አሕዛብ ርኩሰት ለይተው ወደ እነርሱ መጥተው የነበሩት ሁሉ በሉት።


“ሁሉንም በአንድ ጊዜ ስለማጠፋቸው ከዚህ ማኅበር መካከል ተለዩ።”


“ከዚህ ማኅበር መካከል ርቃችሁ ገለል በሉ፥ እኔም በአንድ ጊዜ አጠፋቸዋለሁ።” በግምባራቸውም ወድቀው ሰገዱ።


ስለዚህ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ክብር እንደ ተቀበላችሁ እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ።


በዋዘኞች ጉባኤ አልተቀመጥኩም አልተደሰትኩምም፤ ቁጣን ሞልተህብኛልና እጅህ በእኔ ላይ ስለ ሆነ ለብቻዬ ተቀመጥሁ።


ሰኰናው ስንጥቅ የሆነውን፥ ለሁለት የተከፈለውንና የሚያመሰኳውንም እንስሳ ሁሉ ትበላለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች