1 ሳሙኤል 26:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ሳኦል ተነሣ፤ ዳዊትን ፍለጋ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ከእስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን ይዞ ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሳኦል ተነሣ፤ ከእስራኤል የተመረጡትን ሦስት ሺሕ ሰዎችን ይዞ፣ ዳዊትን ፍለጋ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ወረደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም በፍጥነት ተነሥቶ በእስራኤል ምርጥ የሆኑትን ሦስት ሺህ ወታደሮች በማስከተል ዳዊትን ለመፈለግ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ሄደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ተነሥቶ ዳዊትን በዚፍ ምድረ በዳ ይሻ ዘንድ ከእስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን ይዞ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ተነሥቶ ዳዊትን በዚፍ ምድረ በዳ ይሻ ዘንድ ከእስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺህ ሰዎች ይዞ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ወረደ። |
ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎች ከእስራኤል መረጠ፤ ሁለቱ ሺህ በማክማስና በተራራማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋር፥ አንዱ ሺህ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ ድንኳኖቻቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።
ስለዚህ ሳኦል ከመላው እስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ “የሜዳ ፍየሎች ዓለት” ወደ ተባለው ቦታ አቅራቢያ ሄደ።