1 ሳሙኤል 22:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም፥ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች መገኘታቸውን በሰማ ጊዜ፥ በጊብዓ ኰረብታ ላይ ታማሪስክ ተብሎ የሚጠራ ዛፍ ሥር፥ ጦሩን በእጁ ይዞ ተቀምጦ ነበር፤ አገልጋዮቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፣ ዳዊትና ከርሱ ጋራ የነበሩ ሰዎች መገኘታቸውን በሰማ ጊዜ፣ በጊብዓ ኰረብታ ላይ በአጣጥ ዛፍ ሥር፣ ጦሩን በእጁ ይዞ ተቀምጦ ነበር፤ ሹማምቱም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዕለታት አንድ ቀን ሳኦል ጦሩን በእጁ እንደ ያዘ በጊብዓ በሚገኝ ኮረብታ ላይ ታማሪስክ ተብሎ በሚጠራ ዛፍ ሥር ተቀምጦ ነበር፤ ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም በዙሪያው ቆመው ነበር፤ በዚህን ጊዜ ዳዊትና ተከታዮቹ በአንድ ስፍራ መኖራቸው ለሳኦል ተነገረው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ያሉበት ቦታ እንደ ታወቀ ሰማ። ሳኦልም በራማ በሚገኘው በመሰማርያው ቦታ በኮረብታው ላይ ተቀምጦ በእጁም ጦር ይዞ ነበር፤ ብላቴኖቹም ሁሉ በአጠገቡ ቆመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንደ ተገለጡ ሰማ። ሳኦልም በጊብዓ በአጣጥ ዛፍ በታች በኮረብታው ላይ ተቀምጦ በእጁም ጦር ይዞ ነበር፥ ባሪያዎቹም ሁሉ በአጠገቡ ቆመው ነበር። |
እርሷም በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር፥ በራማና በቤቴል መካከል ካለው የዲቦራ ዘንባባ ዛፍ ሥር ተቀምጣ ትፈርድ ነበር፤ እስራኤላውያንም ለፍርድ ወደ እርሷ ይመጡ ነበር።
በማግስቱም ከእግዚአብሔር የታዘዘ ክፉ መንፈስ ሳኦልን ተቆራኘው፥ ሳኦል በቤቱ ሆኖ እንደ እብድ ይለፈልፍ ነበር፤ በዚህ ጊዜ ዳዊት በየእለቱ እንደሚያደርገው ሁሉ በገና ሲደረድር ነበር። ሳኦል በእጁ ጦር ይዞ ነበር።