Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 22:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሳኦ​ልም ዳዊ​ትና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ሰዎች ያሉ​በት ቦታ እንደ ታወቀ ሰማ። ሳኦ​ልም በራማ በሚ​ገ​ኘው በመ​ሰ​ማ​ር​ያው ቦታ በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ተቀ​ምጦ በእ​ጁም ጦር ይዞ ነበር፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹም ሁሉ በአ​ጠ​ገቡ ቆመው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሳኦልም፣ ዳዊትና ከርሱ ጋራ የነበሩ ሰዎች መገኘታቸውን በሰማ ጊዜ፣ በጊብዓ ኰረብታ ላይ በአጣጥ ዛፍ ሥር፣ ጦሩን በእጁ ይዞ ተቀምጦ ነበር፤ ሹማምቱም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ሳኦልም፥ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች መገኘታቸውን በሰማ ጊዜ፥ በጊብዓ ኰረብታ ላይ ታማሪስክ ተብሎ የሚጠራ ዛፍ ሥር፥ ጦሩን በእጁ ይዞ ተቀምጦ ነበር፤ አገልጋዮቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከዕለታት አንድ ቀን ሳኦል ጦሩን በእጁ እንደ ያዘ በጊብዓ በሚገኝ ኮረብታ ላይ ታማሪስክ ተብሎ በሚጠራ ዛፍ ሥር ተቀምጦ ነበር፤ ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም በዙሪያው ቆመው ነበር፤ በዚህን ጊዜ ዳዊትና ተከታዮቹ በአንድ ስፍራ መኖራቸው ለሳኦል ተነገረው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሳኦልም ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንደ ተገለጡ ሰማ። ሳኦልም በጊብዓ በአጣጥ ዛፍ በታች በኮረብታው ላይ ተቀምጦ በእጁም ጦር ይዞ ነበር፥ ባሪያዎቹም ሁሉ በአጠገቡ ቆመው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 22:6
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብ​ር​ሃ​ምም በዐ​ዘ​ቅተ መሐላ አጠ​ገብ የተ​ምር ዛፍን ተከለ፤ በዚ​ያም የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙን አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠራ።


እር​ስ​ዋም በኤ​ፍ​ሬም ተራራ በቤ​ቴ​ልና በኢ​ያማ መካ​ከል “የዲ​ቦራ ዘን​ባባ” ተብሎ በሚ​ጠ​ራው ዛፍ ሥር ተቀ​ምጣ ነበር፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እር​ስዋ ለፍ​ርድ ይወጡ ነበር።


ሳኦ​ልም በመ​ጌ​ዶን ባለው በሮ​ማኑ ዛፍ በታች በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ረው ሕዝብ ስድ​ስት መቶ የሚ​ያ​ህል ሰው ነበረ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በነ​ጋው ሳኦ​ልን ክፉ መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያዘው፤ በቤ​ቱም ውስጥ ትን​ቢት ተና​ገረ። ዳዊ​ትም በየ​ቀኑ ያደ​ርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦ​ልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።


ሳኦ​ልም ጦሩን ይዞ በቤቱ ተቀ​ምጦ ሳለ ክፉ መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያዘው። ዳዊ​ትም በእጁ በገና ይመታ ነበር።


ሳኦ​ልም ሊገ​ድ​ለው በዮ​ና​ታን ላይ ጦሩን አነሣ፤ ዮና​ታ​ንም አባቱ ዳዊ​ትን ይገ​ድ​ለው ዘንድ ያች ክፉ ነገር እንደ ተቈ​ረ​ጠች ዐወቀ።


አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወሰዱ፤ በኢ​ያ​ቢ​ስም ባለው የእ​ርሻ ቦታ ቀበ​ሩ​አ​ቸው፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች