የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 22:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሁንም ከእኔ ጋር ቆይ፤ አትፍራ፤ የአንተን ሕይወት የሚፈልግ የእኔን ሕይወት ይፈልጋል። አብረኸኝ በሰላም ትኖራለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁንም ከእኔ ጋራ ቈይ፤ አትፍራ፤ የአንተን ሕይወት የሚፈልግ የእኔን ሕይወት የሚፈልግ ነውና። ዐብረኸኝ በሰላም ትኖራለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንተ ግን ከእኔ ጋር ኑር፤ አይዞህ አትፍራ፤ በእርግጥ ሳኦል አንተንም እኔንም ለመግደል ይፈልጋል፤ ነገር ግን አንተ ከእኔ ጋር በሰላም ትኖራለህ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእኔ ጋር ተቀ​መጥ፤ አት​ፍራ፤ ለእኔ ነፍስ የደ​ኅ​ን​ነት ቦታን እን​ደ​ም​ፈ​ልግ ለአ​ን​ተም ነፍስ የደ​ኅ​ን​ነት ቦታን እፈ​ል​ጋ​ለ​ሁና፥ ከእ​ኔም ጋር ተጠ​ብ​ቀህ ትኖ​ራ​ለህ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነፍሴን የሚፈልግ የአንተን ነፍስ ይፈልጋልና፥ ከእኔም ጋር ተጠብቀህ ትኖራለህና በእኔ ዘንድ ተቀመጥ፥ አትፍራ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 22:23
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊትም፥ “አትፍራ፤ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል ቸርነት አደርግልሃለሁ። የአባትህን የሳኦልን ምድር በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም ከማዕዴ ትበላለህ” አለው።


ስለዚህ ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር አሴረ፤ እነርሱም አዶንያስን ደገፉት።


ንጉሥ ሰሎሞን ካህኑን አብያታርን፤ “ወደ ትውልድ አገርህ ወደ ዐናቶት ሂድ፤ አንተ በሞት ልትቀጣ ይገባህ ነበር፤ ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ትሸከም ስለ ነበርክ ከእርሱም ጋር የመከራው ሁሉ ተካፋይ ስለ ነበርክ እኔ አሁን አልገድልህም” አለው።


“በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችኋልም፤ ስለ ስሜም በሕዝቦች ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።


‘ባርያ ከጌታው አይበልጥም፤’ ብዬ የነገርኋችሁን ቃል አስቡ። እኔን ካሳደዱኝ እናንተን ደግሞ ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌንም ከጠበቁ ቃላችሁን ደግሞ ይጠብቃሉ።


ከእነርሱ ጋር በዓለም ሳለሁ የሰጠኸኝን እኔ በስምህ እጠብቃቸው ነበር፤ ጠበቅኋቸውም፤ የመጽሐፉም ቃል እንዲፈጸም ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።


ይህም “ከእነዚህ ከሰጠኸኝ አንዱን እንኳን አላጠፋሁም” ያለው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።


እርሱም፥ “አትፍራ፤ አባቴ ሳኦል እጁን በአንተ ላይ አያሳርፍም፤ በእስራኤል ላይ ትነግሣለህ፤ እኔም ካንተ ቀጥዬ ሁለተኛ ሰው እሆናለሁ፤ ይህንም አባቴ ሳኦል እንኳ ያውቀዋል” አለው።