1 ሳሙኤል 15:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ሳኦል አማሌቃውያንን ከኤውላጥ አንሥቶ በምሥራቅ ግብጽ እስካለው እስከ ሱር ድረስ ወጋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሳኦል አማሌቃውያንን ከኤውላጥ አንሥቶ በምሥራቅ ግብጽ እስካለው እስከ ሱር ድረስ ወጋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል ከሐዊላ ጀምሮ በግብጽ ምሥራቅ እስከምትገኘው እስከ ሹር በሚያደርሰው መንገድ ሁሉ ዐማሌቃውያንን ድል አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ በግብፅ ፊት እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ በግብጽ ፊት እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው። |
ዘሮቹም ከግብጽ በስተ ምሥራቅ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ በሐዊላና በሹር መካከል ሲሰፍሩ፤ የኖረውም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት በተቃርኖ ነበር።
በዚያ ጊዜም ዳዊትና ሰዎቹ ወጥተው ጌሪሹራውያንን፥ ጌዛውያንንና አማሌቃውያንን ወረሩ። እነዚህ ሕዝቦች ከጥንት ጀምሮ፥ እስከ ሱርና እስከ ግብጽ ባለው ምድር ላይ ይኖሩ ነበር።
በሦስተኛው ቀን ዳዊትና ሰዎቹ ጺቅላግ ደረሱ፤ በዚህ ጊዜ አማሌቃውያን ደቡቡን አገርና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ ጺቅላግንም ወግተው አቃጥለው ነበር።