1 ሳሙኤል 15:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ቄናውያንን፥ “ከእነርሱ ጋር እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን ራቁ፤ ተለዩአቸውም፤ ምክንያቱም እናንተ እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ቸርነት አድርጋችሁላቸዋልና” አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ ቄናውያንን፣ “ከእነርሱ ጋራ እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን ራቁ፤ ተለዩአቸውም፤ እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ፣ ቸርነት አድርጋችሁላቸዋልና” አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ቸርነት ስላደረጋችሁላቸው እናንተን ከአማሌቃውያን ጋር እንዳላጠፋ ከዐማሌቃውያን ተለይታችሁ ሂዱ” ብሎ ሳኦል ለቄናውያን ነገራቸው። እነርሱም ከዐማሌቃውያን ተለይተው ሄዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ቄኔዎናውያንን፥ “ከእነርሱ ጋር እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን መካከል ተነሥታችሁ ሂዱ፤ ከግብፅ በወጡ ጊዜ ለእስራኤል ልጆች ቸርነት አድርጋችኋልና” አላቸው። ቄኔዎናውያንም ከአማሌቃውያን መካከል ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦል ቄናውያንን፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፥ ከግብጽ በወጡ ጊዜ ለእስራኤል ልጆች ቸርነት አድርጋችኋልና ከአማሌቅ ጋር እንዳላጠፋችሁ ከመካከላቸው ውረዱ አላቸው፥ ቄናውያንም ከአማሌቃውያን መካከል ሄዱ። |
ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?”
በያቤጽም የተቀመጡ የጸሐፊዎች ወገኖች፤ ቲርዓውያን፥ ሺምዓታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው።
አሁንም እመክርሃለሁና ቃሌን ስማ፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ አንተ በእግዚአብሔር ፊት ሕዝቡን አቅርብ፥ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አቅርብ፤
የቄናዊው የሙሴ አማት ዘሮች ከይሁዳ ሰዎች ጋር በመሆን ከዘንባባዋ ከተማ ተነሥተው፥ ዓራድ አጠገብ በኔጌብ ውስጥ በይሁዳ ምድረ በዳ ካሉት ሕዝቦች ጋር አብረው ሄዱ፥ እዚያም ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ።
በዚያን ጊዜ ቄናዊው ሔቤር፥ ዐማች የአባብ ልጆች ከሆኑት ከሌሎቹ ቄናውያን ተለይቶ በቃዴስ አጠገብ ጻዕናይም ከተባለ ቦታ ከሚገኘው ባሉጥ ዛፍ አጠገብ ድንኳኑን ተክሎ ነበር።
አኪሽም፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ሲል በጠየቀው ጊዜ ዳዊት፥ “የዘመትነው በይሁዳ፥ ወይም በይራሕመኤላውያን፥ ወይም በቄናውያን ላይ ነው” እያለ ይመልስለት ነበር።