1 ቆሮንቶስ 7:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በመሻት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ካልቻሉ ያግቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ራሳቸውን መግዛት ካልቻሉ ያግቡ፤ በምኞት ከመቃጠል ማግባት ይሻላልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በሥጋ ምኞት ከመቃጠል ይልቅ ማግባት የተሻለ ነውና ራሳቸውን መቈጣጠር ቢያቅታቸው ያግቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መታገሥ ባይችሉ ግን ያግቡ፤ በፍትወት ከመቃጠል ማግባት ይሻላልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ። |
ብታገባ ግን ኃጢአት አትሠራም፤ ድንግሊቱም ብታገባ ኃጢአት አትሠራም፤ ነገር ግን እንዲህ በሚያደርጉ በሥጋቸው ላይ መከራ ይገጥማቸዋል፤ እኔም ከዚያ ባስጣልኳችሁ ነበር።
ዳሩ ግን አንድ ሰው በእጮኛው ላይ መልካም አለማድረጉን ቢያስብ፥ እጮኛውም ዕድሜዋ ለጋብቻ ከደረሰ፥ ሊያገባም ከፈቀደ፥ የወደደውን ያድርግ፤ ኃጢአት የለበትም፤ ይጋቡ።
እንግዲህ ወጣት መበለታት እንዲያገቡ፥ ልጆችንም እንዲወልዱ፥ እያንዳንዳቸውም ቤተሰቦቻቸውን እንዲያስተዳድሩ እፈቅዳለሁ፤ በዚህም ተቃዋሚ የሚሳደብበትን ምንም ዓይነት ሰበብ እንዳይሰጡት ነው፤