መጽሐፈ ጦቢት 14:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቱም እንደ ነገረው ሳይሞት የነነዌን ጥፋት ሰማ። ናቡከደነፆርና አሕሻዊሮስም የነነዌን ጥፋት ሰምተው ደስ አላቸው። የጦቢትና የልጁ የጦብያ ነገር ተፈጸመ። ለእግዚአብሔር ለዘለዓለም ክብር ምስጋና ይግባው አሜን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመሞቱ በፊት የነነዌን መጥፋት አየ፥ የነነዌ ሰዎች በሜዶን ንጉሥ በሳያቅሳሬስ ተማርከው ወደ ሜዶን ሲመጡ አየ። በነነዌያውያን እና በአሶራውያን ላይ ስላወረደው ቅጣት ሁሉ እግዚአብሔርን ባረከ። ከመሞቱ በፊት በነነዌ በደረሰው ጥፋት ተደሰተ፥ ጌታ እግዚአብሔርንም ለዘለዓለም ዓለም ባረከ። አሜን። |