ዘኍል 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመቅደስም ውስጥ የሚያገለግሉበትን የማገልገያውን ዕቃ ሁሉ ይውሰዱ፤ በሰማያዊዉም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡት፤ በአቆስጣም ቍርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፤ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዲሁም በመቅደሱ ውስጥ ለአገልግሎት የሚሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ ወስደው በሰማያዊ ጨርቅ በአቆስጣ ቍርበት በመሸፈን በመሸከሚያው ሳንቃ ላይ ያስቀምጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቅደስም ውስጥ የሚገለገሉባቸውን የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ይውሰዱ፥ በሰማያዊውም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡአቸው፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑአቸው፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመቅደሱ መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች ሁሉ ወስደው በሰማያዊ ጨርቅ ይሸፍኑአቸው፤ የለፋ ስስ ቊርበት ደርበውም በመሸከሚያው ተራዳ ላይ ያኑሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመቅደስም ውስጥ የሚያገልግሉበትን የማገልገያውን ዕቃ ሁሉ ይውሰዱ፥ በሰማያዊውም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡት፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት። |
ከእነርሱ አንዳንዶቹ በአገልግሎቱ ዕቃዎች በመቅደሱ ዕቃ ሁሉ፥ በመልካሙም ዱቄት፥ በወይን ጠጁም፥ በዘይቱም፥ በዕጣኑም፥ በሽቱውም ላይ ሹሞች ነበሩ።
ኪራምም ምንቸቶቹንና መጫሪያዎቹን፥ በመሠዊያው ቤት ያሉ ማንኪያዎችንና የመገልገያውን ዕቃ ሁሉ ሠራ። ኪራምም ለንጉሡ ለሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት የሠራውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።
የእግር መታጠቢያዎችን፥ የእጅ መታጠቢያዎችን፥ ጋኖችን፥ የሥጋ ማውጫ ሜንጦዎችንና ኪራም የሠራውን ሥራ ሁሉ ከንጹሕ ናስ ሠርቶ ለንጉሡ ለሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት አቀረበለት።
ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን ዕቃ ሁሉ፥ የወርቁንም መሠዊያ፥ ኅብስተ ገጽ የነበረባቸውን ገበታዎች ሠራ።
ውስጠኛው የእግዚአብሔር ቤት ደጅና ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ የሚወስደው የውስጠኛውም የቤተ መቅደሱ ደጆች የወርቅ ነበሩ። እንዲሁም ሰሎሞን ስለ እግዚአብሔር ቤት የሠራው ሥራ ሁሉ ተፈጸመ።
በወርቁም መሠዊያ ላይ ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በአቆስጣም ቍርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፤ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።
በላዩም የአቆስጣውን ቍርበት መሸፈኛ ያድርጉበት፤ ከእርሱም በላይ ሁለንተናው ሰማያዊ የሆነ መጐናጸፊያ ያግቡበት፤ መሎጊያዎቹንም ያግቡበት።
በኅብስተ ገጹ ገበታ ላይም ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በእርሱም ላይ ወጭቶቹን፥ ጭልፋዎቹንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ለማፍሰስም መቅጃዎቹን ያድርጉበት፤ ሁልጊዜም የሚኖር ኅብስት በእርሱ ላይ ይሁን።
ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፤ የሚያበሩባትንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎችዋንም፥ መኰስተሪያዎችዋንም፥ የኵስታሪ ማድረጊያዎችዋንም፥ እርስዋንም ለማገልገል የዘይቱን ማሰሮዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤