ማቴዎስ 21:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትቶአቸውም ከከተማ ወደ ቢታንያ ወጣ፤ በዚያም አደረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትቷቸው ከከተማው ወጣ፤ ወደ ቢታንያም ሄዶ በዚያው ዐደረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትቶአቸውም ከከተማ ወጥቶ ወደ ቢታንያ ሄደ፤ በዚያም አደረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትቶአቸውም ከከተማ ወጥቶ ቢታንያ ወደምትባል መንደር ሄደ፤ በዚያም ዐደረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትቶአቸውም ከከተማ ወደ ቢታንያ ወጣ በዚያም አደረ። |
ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደስ ገባ፤ ዘወር ብሎም ሁሉን ከተመለከተ በኋላ፥ ጊዜው መሽቶ ስለ ነበረ ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ።
እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ የናርዶስ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፤ ብልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።