የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሉቃስ 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ካህ​ናት እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉት የሚ​ያ​ጥ​ን​በት ጊዜ ደረሰ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደ​ስም ገባ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሥርዐተ ክህነቱ መሠረት፣ ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን በዕጣ ተመረጠ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንደ ካህናት አሠራር ልማድ ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ዕጣን ለማጠን ዕጣ ደረሰው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት።

ምዕራፉን ተመልከት



ሉቃስ 1:9
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ን​በ​ረም ልጆች አሮ​ንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮ​ንም ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን የተ​ቀ​ደሰ ይሆን ዘንድ ተመ​ረጠ፤ እር​ሱና ልጆቹ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያጥ​ኑና ያገ​ለ​ግሉ ነበር፤ በስ​ሙም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይባ​ርኩ ነበር።


አሮ​ንና ልጆቹ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕ​ጣ​ኑም መሠ​ዊያ ላይ ያጥኑ ነበር።


ነገር ግን በበ​ረታ ጊዜ ለጥ​ፋት ልቡ ታበየ፤ አም​ላ​ኩ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደለ፤ በዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅ​ደስ ገባ።


አሁ​ንም በፊቱ ትቆ​ሙና ታገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥ​ኑ​ለ​ትም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መር​ጦ​አ​ች​ኋ​ልና ቸል አት​በሉ።”


እንደ ቆሬና ከእ​ር​ሱም ጋር እንደ ተቃ​ወ​ሙት ሰዎች እን​ዳ​ይ​ሆን፥ ከአ​ሮን ልጆች ያል​ሆነ ሌላ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣን ያጥን ዘንድ እን​ዳ​ይ​ቀ​ርብ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እንደ ተና​ገ​ረው፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ አደ​ረ​ጋ​ቸው።


ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ።


ሥር​ዐቱ፥ ዝግ​ጅ​ቱም እን​ዲህ ነበር፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪ​ቱም ድን​ኳን በየ​ጊ​ዜው አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውን ይፈ​ጽሙ ዘንድ፥ ካህ​ናት ዘወ​ትር ይገቡ ነበር።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ ካህን ይሆ​ነኝ ዘንድ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዬም ላይ ይሠዋ ዘንድ፥ ዕጣ​ን​ንም ያጥን ዘንድ፥ ኤፉ​ድ​ንም በፊቴ ይለ​ብስ ዘንድ፥ የአ​ባ​ት​ህን ቤት ለእኔ መረ​ጥ​ሁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች የእ​ሳት ቍር​ባን ሁሉ ስለ ምግብ ለአ​ባ​ትህ ቤት ሰጠሁ።