የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 24:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከዚ​ያም በኋላ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ወደ ባሕ​ሩም ገባ​ችሁ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና በፈ​ረ​ሶች እስከ ኤር​ትራ ባሕር ድረስ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አባቶቻችሁን ከግብጽ ባወጣኋቸው ጊዜ፣ ወደ ባሕሩ መጣችሁ፤ ግብጻውያንም በሠረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ቀይ ባሕር ድረስ ተከታተሏቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አባቶቻችሁንም ከግብጽ አወጣኋቸው፥ ወደ ባሕሩም ደረሳችሁ፤ ግብፃውያንም አባቶቻችሁን በሰረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ኤርትራ ባሕር ድረስ አባረሩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ባወጣኋቸው ጊዜ ወደ ባሕር ደረሱ፤ ግብጻውያንም በሠረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ቀይ ባሕር ድረስ ባሳደዱአቸው ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አባቶቻችሁንም ከግብፅ አወጣኋቸው፥ ወደ ባሕሩም ደረሳችሁ፥ ግብፃውያንም አባቶቻችሁን በሰረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ኤርትራ ባሕር ድረስ አባረሩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 24:6
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከፊ​ታ​ቸ​ውም ባሕ​ሩን ከፈ​ልህ፤ በባ​ሕ​ሩም መካ​ከል በደ​ረቅ ዐለፉ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውን ግን ድን​ጋይ በጥ​ልቅ ውኃ እን​ዲ​ጣል በቀ​ላይ ውስጥ ጣል​ሃ​ቸው።


እኛ ሕዝ​ብህ ግን፥ የማ​ሰ​ማ​ሪ​ያ​ህም በጎች፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እና​መ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለን፤ ለልጅ ልጅም ምስ​ጋ​ና​ህን እን​ና​ገ​ራ​ለን።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከራ​ምሴ ተነ​ሥ​ተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከጓዝ ጋር ካሉት ሌላ ስድ​ስት መቶ ሺህ ሰው የሚ​ያ​ህል እግ​ረኛ ነበረ።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ቸው።


ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁ፥ በፊትህም ሙሴንና አሮንን ማርያምንም ልኬልህ ነበር።


እር​ሱም አርባ ዘመን በግ​ብፅ ሀገ​ርና በኤ​ር​ትራ ባሕር፥ በበ​ረ​ሃም ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድንቅ ሥራን እየ​ሠራ አወ​ጣ​ቸው።


በደ​ረቅ ምድር እንደ መሄድ የኤ​ር​ት​ራን ባሕር በእ​ም​ነት ተሻ​ገ​ሩ​አት፤ የግ​ብፅ ሰዎች ግን ሲሞ​ክሩ ሰጠሙ።