Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 24:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ባወጣኋቸው ጊዜ ወደ ባሕር ደረሱ፤ ግብጻውያንም በሠረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ቀይ ባሕር ድረስ ባሳደዱአቸው ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አባቶቻችሁን ከግብጽ ባወጣኋቸው ጊዜ፣ ወደ ባሕሩ መጣችሁ፤ ግብጻውያንም በሠረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ቀይ ባሕር ድረስ ተከታተሏቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አባቶቻችሁንም ከግብጽ አወጣኋቸው፥ ወደ ባሕሩም ደረሳችሁ፤ ግብፃውያንም አባቶቻችሁን በሰረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ኤርትራ ባሕር ድረስ አባረሩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ከዚ​ያም በኋላ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ወደ ባሕ​ሩም ገባ​ችሁ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና በፈ​ረ​ሶች እስከ ኤር​ትራ ባሕር ድረስ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አባቶቻችሁንም ከግብፅ አወጣኋቸው፥ ወደ ባሕሩም ደረሳችሁ፥ ግብፃውያንም አባቶቻችሁን በሰረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ኤርትራ ባሕር ድረስ አባረሩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 24:6
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እስራኤላውያን በደረቅ ምድር እንደሚሻገሩ ሆነው ቀይ ባሕርን የተሻገሩት በእምነት ነው፤ ግብጻውያን ግን እንዲሁ ለማድረግ በሞከሩ ጊዜ ሁሉም ሰጠሙ።


በግብጽና በቀይ ባሕር ድንቆችንና ተአምራትን በማድረግ ሕዝቡን አውጥቶ አርባ ዓመት የመራቸው ይህ ሙሴ ነበር።


ከግብጽ አወጣሁህ፤ ከባርነት ምድርም ታደግኹህ፤ ሙሴን፥ አሮንንና ማርያምን በፊትህ መሪዎች አድርጌ ሰጠሁህ።


ባሕሩን ከፍሎ በመካከሉ አሳለፋቸው፤ ውሃው እንደ ግንብ እንዲቆም አደረገ።


ባሕሩን በፊታቸው ለሁለት ከፈልክ፤ በደረቅ ምድርም ተሻገሩ፤ ድንጋይ ወደ ጥልቅ ባሕር እንደሚጣል፥ እነርሱን ያሳድዱ የነበሩትንም ወደ ጥልቁ ጣልካቸው።


በዚያን ቀን እግዚአብሔር መላውን የእስራኤል ሕዝብ በክፍል በክፍል ከግብጽ ምድር መርቶ አወጣ።


እስራኤላውያንም ከራምሴ ተነሥተው ወደ ሱኮት ለመሄድ በእግር ጒዞ ጀመሩ፤ የሰዎቹም ብዛት ሴቶችና ልጆች ሳይቈጠሩ ስድስት መቶ ሺህ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች