ኢያሱ 10:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበርና እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ዕለት ከዚያ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ አልነበረም፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ተዋግቶ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ለእስራኤል ይዋጋ ነበረና ጌታ የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት፥ እንደዚያ ያለ ቀን፥ ከዚያም በፊት ሆነ ከዚያ ወዲህ ታይቶ አይታወቅም፤ በእርግጥም እግዚአብሔር ከእስራኤል ጐን ተሰልፎ ይዋጋላቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበረና እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም። |
የሰረገሎቹንም መንኰራኵር አሰረ፤ ወደ ጭንቅም አገባቸው፤ ግብፃውያንም፥ “እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ” አሉ።
እነሆ፥ በአባትህ የጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ ከፀሐይ ጋራ የወረደውን በደረጃዎች ያለውን ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ።” ፀሐይም በጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ የወረደበት ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ብትኖራችሁ ይህችን ሾላ ከሥርሽ ተነቅለሽ በባሕር ውስጥ ተተከዪ ብትሉአት ትታዘዝላችኋለች።”
በፊታችሁ የሚሄደው አምላካችሁ እግዚአብሔር፥ በግብፅ ምድር እንዳደረገላችሁ ሁሉ፥ ስለ እናንተ አብሮአችሁ ይዋጋል፤
የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤል ስለ ተዋጋላቸው ኢያሱ እነዚህን ነገሥታት ሁሉ ምድራቸውንም በአንድ ጊዜ ያዘ።
እናንተም አምላካችን እግዚአብሔር በፊታችሁ ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ስለ እናንተ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ ስለ እናንተ የተዋጋ እርሱ አምላካችን እግዚአብሔር ነው።