Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 10:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት፥ እንደዚያ ያለ ቀን፥ ከዚያም በፊት ሆነ ከዚያ ወዲህ ታይቶ አይታወቅም፤ በእርግጥም እግዚአብሔር ከእስራኤል ጐን ተሰልፎ ይዋጋላቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ዕለት ከዚያ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ አልነበረም፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ተዋግቶ ነበርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ጌታ ለእስራኤል ይዋጋ ነበረና ጌታ የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ይዋጋ ነበ​ርና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ውን ቃል የሰ​ማ​በት እን​ደ​ዚያ ያለ ቀን ከዚ​ያም በፊት ከዚ​ያም በኋላ አል​ነ​በ​ረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበረና እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 10:14
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዓይናችሁ እያያችሁ በግብጽ እንዳደረገላችሁ ለእናንተ የሚዋጋው በፊታችሁ የሚሄደው አምላካችሁ እግዚአብሔር ነው።


እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፤ እናንተ ማድረግ የሚገባችሁ ጸጥ ብላችሁ ሁኔታውን መጠበቅ ብቻ ነው።”


ኢያሱ እነዚህን ነገሥታትና ግዛቶቻቸውን ሁሉ በአንድ ዘመቻ ድል ያደረገው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋላቸው ስለ ነበረ ነው።


አምላካችን እግዚአብሔር እናንተን ለመርዳት በእነዚህ ሕዝቦች ላይ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ተዋግቶላችኋል፤


ጌታ ኢየሱስም “የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያኽል እምነት ቢኖራችሁ ይህን የሾላ ዛፍ ‘ከዚህ ተነቅለህ በባሕር ውስጥ ተተከል!’ ብትሉት ይታዘዝላችኋል” አላቸው።


ንጉሥ አካዝ ባሠራው የመወጣጫ ደረጃ ላይ የሚያርፈውን ጥላ እግዚአብሔር እንደገና ዐሥር ደረጃዎችን አልፎ ወደ ኋላ እንዲመለስ ያደርገዋል።” ጥላውም ዐሥር ደረጃዎችን አልፎ ወደ ኋላ ተመለሰ።


ከዚህ በኋላ ኢያሱና ሠራዊቱ በጌልገላ ወደ ነበረው ሰፈር ተመለሱ።


እግዚአብሔር የሠረገላዎቻቸውን መንኰራኲሮች ከመሬት ጋር ስላጣበቀባቸው ሠረገሎቻቸውን ነድተው ማንቀሳቀስ አልቻሉም፤ ግብጻውያንም፥ “እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ረድቶ እኛን እየተዋጋን ነው፤ ስለዚህ ከፊታቸው እንሽሽ!” ተባባሉ።


ከዚያን በኋላ እግዚአብሔር በጦርነት ጊዜ እንደሚዋጋ ሕዝቦችን ለመውጋት ይነሣል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች