የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮሐንስ 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ድው​ዩም መልሶ፥ “አዎን ጌታዬ ሆይ፥ ነገር ግን ውኃዉ በተ​ና​ወጠ ጊዜ ወደ መጠ​መ​ቂ​ያዉ የሚ​ያ​ወ​ር​ደኝ ሰው የለ​ኝም፤ እኔ በም​መ​ጣ​በት ጊዜ ሌላው ቀድ​ሞኝ ይወ​ር​ዳል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሕመምተኛውም መልሶ፣ “ጌታዬ፣ ውሃው በሚናወጥበት ጊዜ ወደ መጠመቂያዪቱ የሚያወርደኝ ሰው የለኝም፤ ለመግባትም ስሞክር ሌላው ይቀድመኛል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሕመምተኛውም “ጌታ ሆይ! ውሃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም፤ ነገር ግን እኔ በመምጣት ላይ እያለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል፤” ብሎ መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሽተኛውም “ጌታ ሆይ! ውሃው በሚንቀሳቀስበት ጊዜ እኔን ወስዶ ወደ ኲሬው የሚያስገባኝ ሰው የለኝም፤ እኔ ልሄድ ስል ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ድውዩም፦ ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት



ዮሐንስ 5:7
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰው​ነቴ በላዬ አለ​ቀ​ች​ብኝ፥ ልቤም በው​ስጤ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ።


እነሆ፥ እነ​ዚህ ኃጥ​ኣን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ሁል​ጊ​ዜም ባለ​ጠ​ግ​ነ​ታ​ቸ​ውን ያጸ​ኗ​ታል፤


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በበ​ጎች በር አጠ​ገብ መጠ​መ​ቂያ ነበ​ረች፤ ስም​ዋ​ንም በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉ​አ​ታል፤ አም​ስት እር​ከ​ኖ​ችም ነበ​ሩ​አት።


በዚ​ያም ዕው​ሮ​ችና አን​ካ​ሶች፥ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም የሰ​ለለ ብዙ ድው​ያን ተኝ​ተው የው​ኃ​ዉን መና​ወጥ ይጠ​ባ​በቁ ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ወደ መጠ​መ​ቂ​ያዉ ወርዶ ውኃ​ዉን በሚ​ያ​ና​ው​ጠው ጊዜ፥ ከው​ኃዉ መና​ወጥ በኋላ በመ​ጀ​መ​ሪያ ወርዶ የሚ​ጠ​መቅ ካለ​በት ደዌ ሁሉ ይፈ​ወስ ነበ​ርና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን ሰው በአ​ል​ጋዉ ተኝቶ ባየ ጊዜ በደዌ ብዙ ዘመን እንደ ቈየ ዐውቆ፥ “ልት​ድን ትወ​ዳ​ለ​ህን?” አለው።


ክር​ስ​ቶ​ስም እና ኀጢ​አ​ተ​ኞች ስን​ሆን ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ይሞት ዘንድ ዘመኑ ሲደ​ርስ መጣ።


በእ​ሽ​ቅ​ድ​ም​ድም ስፍራ የሚ​ሽ​ቀ​ዳ​ደሙ ሁሉ እን​ደ​ሚ​ፋ​ጠኑ አታ​ው​ቁ​ምን? ለቀ​ደ​መው የሚ​ደ​ረ​ግ​ለት ዋጋ አለ፤ እን​ዲሁ እና​ን​ተም እን​ድ​ታ​ገኙ ፈጽ​ማ​ችሁ ሩጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ይፈ​ር​ዳል፤ ስለ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ይራ​ራል፤ በያ​ሉ​በት መሳ​ለ​ቂያ ሆነው እንደ ኖሩ፥ ኀይ​ላ​ቸ​ውም እንደ ደከመ፥ በጠ​ላ​ትም እጅ እንደ ወደቁ አይ​ቶ​አ​ልና።