መጀመሪያይቱ እንደ ሴት አንበሳ ነበረች፤ እንደ ንስርም ክንፍ ነበራት፤ ክንፎችዋም ከእርስዋ እስኪነቀሉ ድረስ አይ ነበር፤ ከምድርም ከፍ ከፍ አለች፤ እንደ ሰውም በእግር ቆመች፤ የሰውም ልብ ተሰጣት።