አቤሜሌክም ኤርምያስ ከላከው ቦታ በቀትር ጊዜ በለሱን አመጣ፤ ጽፍቅ ያለች ዱርንም አገኘ፤ ጥቂትም ያርፍ ዘንድ በጥላዋ ስር ተቀመጠ፤ በለስ ያለባትንም ሙዳይ ተንተርሶ ስድሳ ስድስት ዓመት ተኛ፤ ከመኝታውም አልነቃም።