የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 7:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ሂድ ለባ​ሪ​ያዬ ለዳ​ዊት ንገ​ረው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ የም​ኖ​ር​በ​ትን ቤት አት​ሠ​ራ​ል​ኝም።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ሂድና ባሪያዬን ዳዊትን፣ ‘እንዲህ ብለህ ንገረው፤ እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንተ ነህን? በለው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ሂድና አገልጋዬን ዳዊትን፥ ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘እኔ የምኖርበትን ቤተ መቅደስ የምትሠራልኝ አንተ ነህን?’

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ሂድና ለአገልጋዬ ለዳዊት እኔ ስለ እርሱ የምለውን እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘እኔ የምኖርበትን ቤተ መቅደስ የምትሠራልኝ አንተ ነህን?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሂድ፥ ለባሪዬ ለዳዊት ንገረው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 7:5
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ያም ሌሊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ናታን መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፦


ንጉ​ሡም የለ​ዘቡ ታላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮ​ች​ንና ለቤ​ቱም መሠ​ረት ያል​ተ​ጠ​ረ​በ​ውን ድን​ጋይ ያመጡ ዘንድ አዘዘ።


“ስለ​ዚህ ስለ​ም​ት​ሠ​ራ​ልኝ ቤት በሥ​ር​ዐቴ ብት​ሄድ፥ ፍር​ዴ​ንም ብታ​ደ​ርግ፥ ትመ​ላ​ለ​ስ​ባ​ቸ​ውም ዘንድ ትእ​ዛ​ዞቼን ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ ለአ​ባ​ትህ ለዳ​ዊት የነ​ገ​ር​ሁ​ትን ቃል ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ።


“ሂድ፥ ለአ​ገ​ል​ጋዬ ለዳ​ዊት ንገ​ረው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በው​ስጡ እኖ​ር​በት ዘንድ ቤትን የም​ት​ሠ​ራ​ልኝ አንተ አይ​ደ​ለ​ህም፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን፦ የሰ​ልፍ ሰው ነህና፥ ብዙ ደምም አፍ​ስ​ሰ​ሃ​ልና ስሜ የሚ​ጠ​ራ​በ​ትን ቤት አት​ሠ​ራም ብሎ​ኛል።


እግዚአብሔርን መፍራት በጎ ዕውቀትና ጥበብ ነው። ለሚመልስላትም የክብር መጀመሪያ ናት፥ የዋሃንንም ክብር ትከተላቸዋለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድ​ርም የእ​ግሬ መረ​ገጫ ናት፤ የም​ት​ሠ​ሩ​ልኝ ቤት ምን ዓይ​ነት ነው? የማ​ር​ፍ​በ​ትስ ስፍራ ምን​ድን ነው?