የብረት ልብስ እለብሳለሁ፤ የጦር መወርወርና የቀስትም መንደፍ አይችለኝም ትላለህን? የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔርም የምበቀልህ በጦር መወርወር አይደለም ይላል፤ ነገር ግን ከጦር መወርወርና ከቀስት ንድፈት የሚከፋ ጽኑ የልብ በሽታን፥ እከክንና ቍርጥማትን አመጣብሃለሁ፤