የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ነገሥት 16:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰማው፤ የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ወደ ደማ​ስቆ ወጣ፤ ያዛ​ትም፤ ሕዝ​ብ​ዋ​ንም ወደ ቂር አፈ​ለ​ሳ​ቸው፤ ረአ​ሶ​ን​ንም ገደ​ለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የአሦር ንጉሥም፣ የአካዝን ልመና በመቀበል፤ ደማስቆን አጥቅቶ ያዛት፤ ሕዝቧን ማርኮ ወደ ቂር አፈለሳቸው፤ ረአሶንንም ገደለው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የአካዝን ጥያቄ በመቀበል ቲግላት ፐሌሴር ዘምቶ ደማስቆን በቁጥጥሩ ሥር አደረገ፤ ንጉሥ ረጺንንም ገደለ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ቂር ተብላ ወደምትጠራው ስፍራ ወሰደው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የአካዝን ጥያቄ በመቀበል ቲግላት ፐሌሴር ዘምቶ ደማስቆን በቊጥጥሩ ሥር አደረገ፤ ንጉሥ ረጺንንም ገደለ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ቂር ተብላ ወደምትጠራው ስፍራ ወሰደው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የአሦርም ንጉሥ ሰማው፤ የአሦርም ንጉሥ በደማስቆ ላይ ወጣባት፤ ወሰዳትም፤ ሕዝብዋንም ወደ ቂር አፈለሳቸው፤ ረአሶንንም ገደለ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ነገሥት 16:9
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወልደ አዴ​ርም ንጉ​ሡን አሳን ሰማው፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞች ላይ ሰደደ፤ እነ​ር​ሱም አእ​ዮ​ን​ንና ዳንን፥ አቤ​ል​ማ​ይ​ም​ንና የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም አው​ራጃ ከተ​ሞች ሁሉ መቱ።


አካ​ዝም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ከን​ጉ​ሡና ከአ​ለ​ቆ​ቹም ቤት የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ወሰደ፤ ለአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰጠ፥ ነገር ግን አስ​ጨ​ነ​ቀው እንጂ አል​ረ​ዳ​ውም።


ስለ​ዚህ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሶ​ርያ ንጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ሰጠው፤ እር​ሱም መታው፤ ከእ​ር​ሱም ብዙ ምር​ኮ​ኞ​ችን ወሰደ፤ ወደ ደማ​ስ​ቆም አመ​ጣው። ደግ​ሞም በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ሰጠው፤ እር​ሱም በታ​ላቅ አመ​ታት መታው።


እንደ ሔማት አር​ፋድ፥ እንደ አር​ፋድ ሴፋ​ሩ​ሔም፥ እንደ ሴፋ​ሩ​ሔም ካሌና፥ እንደ ካሌ​ናም ደማ​ስቆ፥ እንደ ደማ​ስ​ቆም ሰማ​ርያ አይ​ደ​ለ​ች​ምን?


ስለ ደማ​ስቆ የተ​ነ​ገረ ቃል። “እነሆ፥ ደማ​ስቆ ከከ​ተ​ሞች መካ​ከል ተለ​ይታ ትጠ​ፋ​ለች፤ ትፈ​ር​ሳ​ለ​ችም።


የኤ​ላ​ምም ሰዎች አፎ​ታ​ቸ​ውን ተሸ​ከሙ፤ በፈ​ረስ የተ​ቀ​መ​ጡና አር​በ​ኞች ሰዎች፥ የአ​ር​በ​ኞ​ችም ሠራ​ዊት ነበሩ።


አቤቱ፥ በእ​ው​ነት የአ​ሦር ነገ​ሥ​ታት ዓለ​ሙን ሁሉ ሀገ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋል፤


ሕፃኑ ክፉን ለመ​ጥ​ላት፥ መል​ካ​ሙን ለመ​ም​ረጥ ሳያ​ውቅ፥ የፈ​ራ​ሃ​ቸው የሁ​ለቱ ነገ​ሥ​ታት ሀገር ባድማ ትሆ​ና​ለች።


“ጡቡ ወደቀ፤ ነገር ግን ኑ፥ ድን​ጋይ እን​ው​ቀር፤ ሾላው ነቀዘ፤ ነገር ግን ፅድን እን​ቍ​ረጥ፤ ለራ​ሳ​ች​ንም ግን​ብን እን​ሥራ።”


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራራ ላይ እር​ሱን በመ​ቃ​ወም የሚ​ነ​ሡ​ትን ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! እና​ንተ ለእኔ እንደ ኢት​ዮ​ጵያ ልጆች አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ምድር፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ከቀ​ጰ​ዶ​ቅያ፥ ሶር​ያ​ው​ያ​ን​ንም ከጕ​ድ​ጓድ ያወ​ጣሁ አይ​ደ​ለ​ምን?