የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 8:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም አሉት፥ “እነሆ፥ አንተ ሸም​ግ​ለ​ሃል፤ ልጆ​ች​ህም በመ​ን​ገ​ድህ አይ​ሄ​ዱም፤ አሁ​ንም እንደ ሌሎች አሕ​ዛብ ሁሉ የሚ​ፈ​ር​ድ​ልን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን።”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም፣ “አንተ አርጅተሃል፤ ልጆችህ ያንተን ፈለግ አይከተሉም፤ ስለዚህ ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሁሉ የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም፥ “አንተ አርጅተሃል፤ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም፤ ስለዚህ ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሁሉ የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እነሆ! አንተ በእርጅና ላይ ነህ፤ ልጆችህም የአንተን መልካም አርአያነት አልተከተሉም፤ ስለዚህ በሌሎች አገሮች እንደሚደረገው እኛን የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆ፥ አንተ ሸምግለሃል፥ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም፥ አሁንም እንደ አሕዛብ ሁሉ የሚፈርድልን ንጉሥ አድርግልን አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 8:5
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ሆኜ አየ​ዋ​ለሁ፤ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ሆኜ እመ​ለ​ከ​ተ​ዋ​ለሁ፤ እነሆ፥ ብቻ​ውን የሚ​ቀ​መጥ ሕዝብ ነው፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል አይ​ቈ​ጠ​ርም።


ከዚ​ያም ወዲያ ንጉሥ ያነ​ግ​ሥ​ላ​ቸው ዘንድ ለመኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከብ​ን​ያም ነገድ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ሰው የቂ​ስን ልጅ ሳኦ​ልን አርባ ዓመት አነ​ገ​ሠ​ላ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ከም​ድ​ያም እጅ አድ​ነ​ኸ​ና​ልና አንተ፥ ልጅ​ህም፥ የልጅ ልጅ​ህም ደግሞ ግዙን” አሉት።


ዛሬ ግን ከመ​ከ​ራ​ች​ሁና ከጭ​ን​ቃ​ችሁ ሁሉ ያዳ​ና​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንቃ​ችሁ፦ ‘እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን’ አላ​ች​ሁት። አሁ​ንም በየ​ነ​ገ​ዳ​ች​ሁና በየ​ወ​ገ​ና​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቁሙ” አላ​ቸው።


አሁ​ንም የመ​ረ​ጣ​ች​ሁ​ትን ንጉሥ እዩ፤ እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉሥ ሰጣ​ችሁ።


የስ​ንዴ መከር ዛሬ አይ​ደ​ለ​ምን? ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጮ​ኻ​ለሁ፤ እር​ሱም ነጐ​ድ​ጓ​ድ​ንና ዝና​ብን ይል​ካል፤ እና​ን​ተም ንጉሥ በመ​ለ​መ​ና​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ክፋት ታላቅ እንደ ሆነ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ታያ​ላ​ች​ሁም።”


አሁ​ንም እነሆ፥ ንጉሡ በፊ​ታ​ችሁ ይሄ​ዳል፤ እኔም አር​ጅ​ቻ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲ​ህም አር​ፋ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ ልጆቼ ከእ​ና​ንተ ጋር ናቸው፤ እኔም ከሕ​ፃ​ን​ነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፊ​ታ​ችሁ ሄድሁ።


ከሦ​ስት ቀንም በፊት የጠፉ አህ​ዮ​ችህ ተገ​ኝ​ተ​ዋ​ልና ልብ​ህን አታ​ስ​ጨ​ን​ቀው። የእ​ስ​ራ​ኤል መል​ካም ምኞት ለማን ነው? ለአ​ን​ተና ለአ​ባ​ትህ ቤት አይ​ደ​ለ​ምን?” አለው።