ዘኍል 23:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 በተራሮች ራስ ላይ ሆኜ አየዋለሁ፤ በኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ እነሆ፥ ብቻውን የሚቀመጥ ሕዝብ ነው፤ በአሕዛብም መካከል አይቈጠርም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ከዐለታማ ተራሮች ጫፍ ሆኜ አየዋለሁ፤ በከፍታዎቹም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ ተለይቶ የሚኖረውን፣ ራሱንም ከሌሎች ሕዝቦች ጋራ የማይቈጥረውን ሕዝብ አያለሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 በተራሮች ራስ ላይ ሆኜ አየዋለሁ፥ በኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ እነሆ፥ ብቻውን የሚቀመጥ ሕዝብ ነው፥ በአሕዛብም መካከል አይቈጠርም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 እኔ እነርሱን ከነዚህ ከፍተኛ አለቶች ላይ ሆኜ አያቸዋለሁ፤ ከኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከታቸዋለሁ፤ እነርሱ ለብቻቸው የሚኖሩ ሕዝብ ናቸው። እነርሱ ከሌሎች ሕዝቦች ይልቅ የተለዩ መሆናቸውን ያውቃሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 በአምቦች ራስ ላይ ሆኜ አየዋለሁ፥ በኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ እነሆ፥ ብቻውን የሚቀመጥ ሕዝብ ነው፥ በአሕዛብም መካከል አይቈጠርም። ምዕራፉን ተመልከት |