የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 24:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም ሰዎ​ቹን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባው ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው በጌ​ታዬ ላይ እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር አደ​ርግ ዘንድ፥ እጄ​ንም እጥ​ል​በት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ያር​ቀው” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊት ሰዎቹን በዚህ ቃል ገሠጻቸው፤ በሳኦል ላይ አደጋ እንዲያደርሱበትም አልፈቀደላቸውም። ሳኦልም ከዋሻው ወጥቶ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለሰዎቹም፥ “ጌታ በቀባው በጌታዬ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ከማድረግና ጌታ የቀባው ስለ ሆነም እጄን በእርሱ ላይ ከማንሣት ጌታ ይጠብቀኝ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህም አባባሉ በሳኦል ላይ አደጋ እንዳይጥሉበት ዳዊት ተከታዮቹን ከለከላቸው። ሳኦልም ከዚያ በመነሣት ከዋሻው ወጥቶ ሄደ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም በዚህ ቃል ሰዎቹን ከለከላቸው፥ በሳኦልም ላይ ይነሡ ዘንድ አልተዋቸውም፥ ሳኦልም ከዋሻው ተነሥቶ መንገዱን ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 24:7
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም፥ “ትገ​ድ​ለው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው ላይ እጅ​ህን ስት​ዘ​ረጋ እን​ዴት አል​ፈ​ራ​ህም?” አለው።


ክፉ ላደ​ረ​ጉ​ብ​ኝም ክፉን መል​ሼ​ላ​ቸው ብሆን፥ ጠላ​ቶቼ ዕራ​ቁ​ቴን ይጣ​ሉኝ።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።


እነ​ሆኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና እርሱ በቀ​ባው ፊት መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ የማ​ንን በሬ ወሰ​ድሁ? የማ​ን​ንስ አህያ ወሰ​ድሁ? ማን​ንስ ሸነ​ገ​ልሁ? በማ​ንስ ላይ ግፍ አደ​ረ​ግሁ? ነጠላ ጫማ እን​ኳን ቢሆን ከማን እጅ መማ​ለጃ ተቀ​በ​ልሁ? መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ እኔ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።”


ከዚ​ያም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የሳ​ኦ​ልን የል​ብ​ሱን ዘርፍ ስለ ቈረጠ የዳ​ዊት ልብ በኀ​ዘን ተመታ።


ዳዊ​ትም በዚህ ቃል ሰዎ​ቹን ከለ​ከ​ላ​ቸው። በሳ​ኦ​ልም ላይ ተነ​ሥ​ተው ይገድ​ሉት ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ቸ​ውም፤ ሳኦ​ልም ከዋ​ሻው ተነ​ሥቶ መን​ገ​ዱን ሄደ።


ጠባ​ይሽ የተ​ባ​ረከ ነው። ወደ ደም እን​ዳ​ል​ገባ፥ እጄ​ንም እን​ዳ​ድን ዛሬ የከ​ለ​ከ​ል​ሽኝ አን​ቺም የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ።


ዛሬም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጄ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶህ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው ላይ እጄን እዘ​ረጋ ዘንድ አል​ወ​ደ​ድ​ሁ​ምና ለሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጽድ​ቁና እንደ እም​ነቱ ፍዳ​ውን ይክ​ፈ​ለው።


ዳዊ​ትም አቢ​ሳን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው ላይ እጁን የሚ​ዘ​ረጋ ንጹሕ አይ​ሆ​ን​ምና አት​ግ​ደ​ለው” አለው።