Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 26:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ዛሬም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጄ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶህ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው ላይ እጄን እዘ​ረጋ ዘንድ አል​ወ​ደ​ድ​ሁ​ምና ለሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጽድ​ቁና እንደ እም​ነቱ ፍዳ​ውን ይክ​ፈ​ለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ጽድቁና እንደ ታማኝነቱ ይክፈለው። እኔ ግን ዛሬ እግዚአብሔር አንተን በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን አላነሣሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ጽድቁና እንደ ታማኝነቱ ይክፈለው። እኔ ግን ዛሬ አንተን ጌታ በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ ጌታ በቀባው ላይ እጄን አላነሣሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ታማኞች ለሆኑ ለደጋግ ሰዎች የመልካም ሥራቸውን ዋጋ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ ዛሬ እግዚአብሔር አንተን በእጄ ጥሎልኝ ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔር መርጦ ያነገሠህን አንተን ልጐዳ አልፈለግሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ዛሬም እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶህ ሳለ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ አልወደድሁምና ለሁሉ እያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ ጽድቁና እንደ እምነቱ ፍዳውን ይክፈለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 26:23
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጽድቄ ይከ​ፍ​ለ​ኛል፤ እንደ እጄ ንጽ​ሕ​ናም ይመ​ል​ስ​ል​ኛል፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽ​ሕና በዐ​ይ​ኖቹ ፊት መለ​ሰ​ልኝ።


በሰ​ማይ ስማ፤ አድ​ር​ግም፤ በባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዳኛ ሁን፤ በበ​ደ​ለ​ኛ​ውም ላይ ፍረድ፤ መን​ገ​ዱ​ንም በራሱ ላይ መል​ስ​በት፤ ጻድ​ቁን አጽ​ድ​ቀው፤ እንደ ጽድ​ቁም ክፈ​ለው።


አም​ላኬ ሆይ፥ ስለ​ዚህ አስ​በኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ወረ​ታ​ዬን አታ​ጥፋ።


ለሰው ሁሉ እንደ ሥራው ይመ​ል​ስ​ለ​ታል፥ ሰው​ንም እንደ መን​ገዱ ያገ​ኘ​ዋል።


እነሆ፥ ዛሬ በዋ​ሻው ውስጥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጄ አሳ​ልፎ እንደ ሰጠህ ዐይ​ንህ አይ​ታ​ለች፤ አን​ተ​ንም እን​ድ​ገ​ድ​ልህ ሰዎች ተና​ገ​ሩኝ፤ እኔ ግን፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀባ ነውና እጄን በጌ​ታዬ ላይ አል​ዘ​ረ​ጋም ብዬ ራራ​ሁ​ልህ።


እነሆ፥ የል​ብ​ስህ ዘርፍ በእጄ እን​ዳለ ተመ​ል​ክ​ተህ ዕወቅ፤ የል​ብ​ስ​ህ​ንም ዘርፍ በቈ​ረ​ጥሁ ጊዜ አል​ገ​ደ​ል​ሁ​ህም፤ ስለ​ዚ​ህም በእጄ ክፋት፥ በደ​ልና ክዳት እን​ደ​ሌለ፥ አን​ተ​ንም እን​ዳ​ል​በ​ደ​ል​ሁህ ዕወቅ፤ አንተ ግን ነፍ​ሴን ልታ​ጠፋ ታጠ​ም​ዳ​ለህ።


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን አለው፥ “እኔ ክፉ በመ​ለ​ስ​ሁ​ልህ ፋንታ በጎ መል​ሰ​ህ​ል​ኛ​ልና አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዛሬ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶኝ ሳለ አል​ገ​ደ​ል​ኸ​ኝ​ምና ለእኔ መል​ካም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ኽ​ልኝ ለእኔ ነገ​ር​ኸኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀ​ባው ላይ እጄን እዘ​ረጋ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ያር​ቀው፤ አሁ​ንም በራሱ አጠ​ገብ ያለ​ውን ጦርና የው​ኃ​ውን መን​ቀል ይዘህ እን​ሂድ፤” አለው።


ዳዊ​ትም መልሶ አለ፥ “የን​ጉሥ ጦር እነሆ፤ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ችም አንድ ይም​ጣና ይው​ሰ​ዳት።


ዳዊ​ትም አቢ​ሳን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው ላይ እጁን የሚ​ዘ​ረጋ ንጹሕ አይ​ሆ​ን​ምና አት​ግ​ደ​ለው” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች