ለመግደል ችሎታ ካለው ሰው ራቅ፤ የሞት ፍርሃት አያድርብህም። ግን ወደሱ ስትቀርብ በጣም ተጠንቀቅ፤ ሊገድልህ ይችላል፤ በወጥመድ መካከል የምትሄድና በከተማይቱ ምሽግ ላይ የምትራመድ መሆንህን አትዘንጋ።
በሞት ከሚቀጡ መኳንንት ፈጽመህ ራቅ፤ ሰውነትህን እንዳታጠፋ የሞት ጥርጥር አያግኝህ፥ ነገር ግን በወጥመድ መካከል እንደምትሄድ፥ በገደልም መካከል እንደምትመላለስ ዕወቅ።