ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ሲራክ 9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)ስለ ሴቶች የተሰጠ ምክር 1 ክፉ ትምህርትን እንዳትማርብህ፥ ባጠገብህ የምተተኛ ሚስትህን አታስቀናት። 2 ኀይልህን እንዳታደክምብህ፥ ለሴት ልብህን አትስጣት። 3 በወጥመድዋ እንዳትያዝ የሌላ ሚስት አታባብል። 4 በዘፈኗ እንዳታስትህ ከዘፋኝ ሴት ጋር አትጫወት። 5 ፈቃዷ እንዳያስትህ ድንግልን አትቈንጥጣት። 6 ርስትህን እንዳታጣ ለአመንዝራ ልቡናህን አትስጣት። 7 በከተማዎቹ መንገድ ዙሪያ አታማትር፤ አደባባይዋም አያስትህ። 8 ከመልከ መልካም ሴት ዐይንህን መልስ፤ የሌላ ሚስትም ደም ግባትዋ አያስጐምጅህ፤ በሴት ደም ግባት የሳቱ ሰዎች ብዙዎች ናቸውና፤ ስለዚህ ነገር ፍቅሯ እንደ እሳት ይነድዳል። 9 ከጐልማሳ ሚስት ጋር አትቀመጥ፤ ልቡናህን ወደ እርሷ እንዳትወስድ፥ ሰውነትህንም በሞት እንዳታሰነካክል በመጠጥ ጊዜ ከእርሷ ጋር አትቀመጥ። 10 ድንገተኛ ወዳጅ እንደ እርሱ አይሆንህምና፥ የቀድሞ ወዳጅህን አትተወው። አዲስ ወዳጅ ጉሽ ጠጅ ነው፤ ቢከርም ግን ደስ ብሎህ ትጠጣዋለህ። 11 እንደሚጠፉ አታውቅምና የኃጥኣን ብልጽግናቸው አያስቀናህ። 12 የክፉዎች ሰዎችም ተድላቸው አያስጐምጅህ፤ እስኪሞቱም ድረስ እንደማይከብሩ ዐስብ። 13 በሞት ከሚቀጡ መኳንንት ፈጽመህ ራቅ፤ ሰውነትህን እንዳታጠፋ የሞት ጥርጥር አያግኝህ፥ ነገር ግን በወጥመድ መካከል እንደምትሄድ፥ በገደልም መካከል እንደምትመላለስ ዕወቅ። 14 የተቻለህን ያህል ለባልንጀራህ መልካም አድርግለት፤ ከጠቢባንም ጋር ተማከር። 15 ጉዳይህም ከዐዋቂዎች ጋር ይሁን፤ ነገርህ ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግ ይሁንልህ። 16 ድሆች ሰዎች በምሳሕ ጊዜ ይኑሩ፤ ክብርህም እግዚአብሔርን በመፍራት ይሁን። 17 ሥራው በብልሃተኛው እጅ ይከናወናል፤ የአሕዛብንም አለቃ በቃሉ ጥበብ ያመሰግኑታል። 18 ተናጋሪ ሰው በከተማው አስፈሪ ነው፥ ከቃሉም የተነሣ ፈጽሞ ይጠላል። |