ሙቀትንም ለማግኘት ወናፍን መንፋት አለብን፤ ፀሐይ ግን ተራሮቹን ሦስት እጥፍ ጊዜ ታነዳቸዋለች፤ እስትንፋሷ የእሳት ነበልባል፥ ጮራዋም አንጸባራቂና ዓይንን የሚያጥበረብር ነው።
ዋዕዩንም እሳት እንደሚነድድባት ምድጃ ያደርጋል፤ ፀሐይ ግን ከሦስት ጊዜ በላይ የበለጠ ተራሮችን ያቃጥላቸዋል። ከእርሱ የሚወጣው እሳታዊ ዋዕይ፥ የሚልከውም ብርሃን ዐይን ያጨልማል፤