Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የጠ​ራች ጠፈ​ርን በህ​ዋው ላይ አጸ​ናት፤ የሰ​ማ​ይም መታ​የት በክ​ብሩ ነው።

2 ብር​ሃ​ኑን ያሳይ ዘንድ ፀሐ​ይን ያወ​ጣል፤ የሰ​ማ​ይም ብር​ሃን ሥር​ዐቱ ድንቅ ነው ።

3 በዋ​ዕ​ዩም ሀገ​ሩን ያቃ​ጥ​ላል፤ ዋዕ​ዩ​ንስ ማን ይቋ​ቋ​መ​ዋል?

4 ዋዕ​ዩ​ንም እሳት እን​ደ​ሚ​ነ​ድ​ድ​ባት ምድጃ ያደ​ር​ጋል፤ ፀሐይ ግን ከሦ​ስት ጊዜ በላይ የበ​ለጠ ተራ​ሮ​ችን ያቃ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል። ከእ​ርሱ የሚ​ወ​ጣው እሳ​ታዊ ዋዕይ፥ የሚ​ል​ከ​ውም ብር​ሃን ዐይን ያጨ​ል​ማል፤

5 የፈ​ጠ​ረው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታላቅ ነው፤ በቃ​ሉም ፈጥኖ ይሄ​ዳል።

6 ጨረ​ቃም ለሁሉ የዘ​መን መለ​ኪያ ናት፤ ለዓ​ለ​ምም ሁሉ ምል​ክት ናት፤ በእ​ር​ስ​ዋም ቀን ይለ​ያል።

7 በጨ​ረ​ቃም የበ​ዓ​ላት ምል​ክት ይታ​ወ​ቃል፤ ሕፀፅ እያ​ደ​ረ​ገች የም​ታ​ልቅ ብር​ሃን እር​ስዋ ናት።

8 ጨረ​ቃስ እንደ ስሟ ናት፤ ዕድ​ገ​ት​ዋም ድንቅ ነው፤ በሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሥር​ዐ​ትም ሕፀ​ፅ​ንና ምላ​ትን ማፈ​ራ​ረ​ቅዋ ድንቅ ነው፤ በሰ​ማይ ሠራ​ዊት መካ​ከ​ልም ታበ​ራ​ለች።

9 የሰ​ማ​ይም ጌጥ የከ​ዋ​ክ​ብት ብር​ሃን ነው። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማይ ለዓ​ለም ያበ​ራሉ።

10 በቅ​ዱ​ሱም ቃል በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ጸን​ተው ይኖ​ራሉ፤ ከሥ​ር​ዐ​ታ​ቸ​ውም ወጥ​ተው አያ​ል​ፉም።

11 ብር​ሃኑ ፈጽሞ ያማረ ነውና፥ ቀስተ ደመ​ና​ውን አይ​ተህ ፈጣ​ሪ​ውን አመ​ስ​ግ​ነው።

12 በሰ​ማይ ይከ​ፈ​ላል፤ ብር​ሃ​ኑም ይከ​በ​ዋል፤ የል​ዑ​ልም እጅ ይከ​ፍ​ለ​ዋል።

13 በት​እ​ዛዙ በረድ ይዘ​ን​ባል፤ መብ​ረ​ቅም በፈ​ቃዱ ፈጥኖ ይወ​ር​ዳል።

14 ስለ​ዚህ ነገር መዛ​ግ​ብ​ቱን ይገ​ል​ጣል፤ ደመ​ና​ትም እንደ ወፎች ይበ​ር​ራሉ።

15 በገ​ና​ና​ነ​ቱም ደመ​ና​ትን ያጸ​ና​ቸ​ዋል፤ የበ​ረድ ድን​ጋ​ይም ይሰ​ባ​በ​ራል።

16 በመ​ጐ​ብ​ኘ​ቱም ተራ​ሮች ይነ​ዋ​ወ​ጣሉ፤ በፈ​ቃ​ዱም የም​ሥ​ራቅ ነፋስ ይነ​ፍ​ሳል።

17 የመ​ብ​ረ​ቁም ድምፅ ምድ​ርን ያስ​ፈ​ራ​ታል፤ የም​ዕ​ራ​ብም ነፋስ ሰው​ነ​ትን ያደ​ር​ቃ​ታል፤ በረ​ድ​ንም እን​ደ​ሚ​በ​ርሩ ወፎች ይበ​ት​ነ​ዋል፤ አወ​ራ​ረ​ዱም እንደ አን​በጣ አወ​ራ​ረድ ነው።

18 የን​ጣ​ቱም ውበት ለዐ​ይን ድንቅ ነው፤ መዝ​ነ​ቡም ለልብ ድንቅ ነው።

19 በረ​ድን እንደ ጨው ያፈ​ስ​ሰ​ዋ​ልና፤ ጉም​ንም በም​ድር ላይ ይበ​ት​ነ​ዋል፤ ውር​ጭም ከረጋ በኋላ እንደ ሻፎ የብ​ርሌ ስባሪ ብልጭ ይላል።

20 የቀ​ዘ​ቀ​ዘው የም​ሥ​ራቅ ነፋ​ስም ይነ​ፍ​ሳል፤ ውር​ጩም በውኃ ላይ ይረ​ጋል፤ በው​ኃው መከ​ማቻ ላይም ይቆ​ማል፤ እንደ ብረት ልብ​ስም በውኃ ላይ ይኖ​ራል፤ ይሸ​ፍ​ና​ታ​ልም።

21 ተራ​ራ​ውን ይበ​ላል፤ ምድረ በዳ​ው​ንም ያቃ​ጥ​ላል፤ ሣሩ​ንም እንደ እሳት ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።

22 የሰው ሁሉ ፈውስ ፈጥኖ የሚ​መጣ ካፊያ ነው፤ ዝና​ብም ወደ ምድር በወ​ረደ ጊዜ ደስ ያሰ​ኛል።

23 በእ​ር​ሱም ምክር ጥልቁ ይደ​ር​ቃል፤ በዚ​ያም ደሴ​ቶ​ችን ተከለ።

24 በባ​ሕ​ርም የሚ​ሄዱ ሰዎች መከ​ራ​ዋን ይና​ገ​ራሉ፥ እኛም ሰም​ተን እና​ደ​ን​ቃ​ለን።

25 በዚ​ያም ሥራው ፈጽሞ ድንቅ ነው። ከብ​ትን መግ​ዛት በየ​ወ​ገኑ ነው።

26 ለበጎ መዓ​ዛም ከእ​ርሱ መሥ​ዋ​ዕት ይሠ​ዋ​ለ​ታል፤ በቃ​ሉም ሁሉ ይደ​ረ​ጋል።

27 ብዙ ነገ​ርን እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ መፈ​ጸ​ምም አን​ች​ልም፤ ነገር ግን የነ​ገሩ ሁሉ መጨ​ረሻ እርሱ ብቻ ነው።

28 ከፍ​ጥ​ረት ሁሉ እርሱ ይበ​ል​ጣ​ልና፤ እር​ሱን ማመ​ስ​ገን ምን ያህል እን​ች​ላ​ለን?

29 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ስ​ፈራ ነው፤ እጅ​ግም ታላቅ ነው፤ ኀይ​ሉም ድንቅ ነው።

30 ጨር​ሳ​ችሁ ማመ​ስ​ገ​ንን አት​ጠ​ነ​ቅ​ቁ​ምና፤ የተ​ቻ​ላ​ች​ሁን ያህል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤ እርሱ ግን ከዚህ ሁሉ በላይ ነው። በፍ​ጹም ኀይ​ላ​ች​ሁም አግ​ን​ኑት፤ አት​ደ​ር​ሱ​በ​ት​ምና እር​ሱን ማመ​ስ​ገ​ንን ቸል አት​በሉ።

31 እር​ሱን አይቶ የሚ​ነ​ግ​ረን ማን ነው? እንደ ገና​ና​ነ​ቱስ መጠን ማን ያገ​ነ​ዋል?

32 የማ​ይ​ታ​የው ከዚህ የሚ​በ​ል​ጠው ፍጥ​ረቱ ብዙ ነው፤ ነገር ግን ያየ​ነው ፍጥ​ረቱ ጥቂት ብቻ ነው።

33 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን ፈጥ​ሯ​ልና፤ ለጻ​ድ​ቃ​ንም ጥበ​ብን ሰጣ​ቸው።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች