በመጀመሪያ በጠመዝማዛ መንገዶች ትወስደዋለች፤ ፍርሃትንና ድንጋጤን ታመጣበታለች፤ እስክታምነው ድረስ በሥርዓቷ ታጠናዋለች፤ በመከራም ትፈትነዋለች።
ከእርሱ ጋር ትሄድ ዘንድ ትቀድማለች፤ ፈጽማም ታስፈራዋለች፥ ሰውነቱን እስክታስገዛና በተግሣጽዋ እስክትፈትነው ድረስ፥ ትገርፈዋለች ታስተምረዋለችም።