እኔ ግን እግሮቼ ሊሰናከሉ፥ በአረማመዴም ልወድቅ ትንሽ ቀረኝ።
እኔ ግን እግሬ ሊሰናከል፣ አዳልጦኝም ልወድቅ ጥቂት ቀረኝ።
በእኔ በኩል ግን እርምጃዎቼ እየተንገዳገዱ፥ እግሮቼም ሊንሸራተቱ ተቃርበዋል።
አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን፥ የተቤዠሃትንም የርስትህን በትር፥ በውስጥዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ ዐስብ።
ዳዊትም ሰሎሞንን እንዲህ አለ፦ “ልጄ ሆይ! እኔ ለአምላኬ ለጌታ ቤት እንድሠራ በልቤ አስቤ ነበር።
ተደላድሎ የተቀመጠ ሰው መከራን ይንቃል፥ እግሩን ያዳለጠውንም ለመገፍተር ተዘጋጅቶአል።
በውኑ የኀዘን እንጉርጉሮዬን ለሰው እናገራለሁን? አለመታገሤ ተገቢ አይደለምን?
በእርግጥም ነፍሴን ከሞት፥ ዓይኔንም ከእንባ፥ እግሬንም ከመሰናከል አድነሃል።
እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፥ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።
እግሮች እንዳይናወጡ አረማመዴን በመንገድህ አጽና።
እኔስ እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፥ ነፍሴንም በጾም አደከምኋት፥ ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ።
አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና፥ አቤቱ አምላኬ፥ አንተ ትሰማኛለህ።
ሐሰትን የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፥ ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው ጌታ ይጸየፋል።
እግሮቼ ተሰናከሉ ባልሁ ጊዜ፥ አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህ ረዳኝ።
በማኅበርና በጉባኤ መካከል ለክፉ ሁሉ ለመዳረግ ጥቂት ቀረኝ።”
ጌታንም ማገልገል ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያገለገሉአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው የተቀመጣችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታገለግሉ እንደሆነ፥ የምታገለግሉትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን ጌታን እናገለግላለን።”
ከዚህም በላይ እኔ ለእናንተ ከመጸለይ ወደ ኋላ በማለት ጌታን እንዳልበድል ይህ ከእኔ ይራቅ፤ እኔ መልካምና ቅን የሆነውን መንገድ አስተምራችኋለሁ።
እርሱ የታማኞቹን እግር ይጠብቃል ሰው በኃይሉ አይበረታምና፥ ኃጥአን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይጣላሉ።