በቸርነት የሚያግዘውንም አያግኝ፥ ለድሀ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።
ማንም ሰው ምሕረት አያድርግለት፤ ለድኻ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።
የሚራራለት ሰው ከቶ አይኑር፤ ድኻ ዐደግ ልጆቹን የሚንከባከባቸው ሰው አይገኝ።
ልጆቹም ከደኅንነት ርቀዋል፥ በበርም ውስጥ ተረግጠዋል፥ የሚደርስላቸውም የለም።
ቀስታቸው ጐበዞችን ይፈጃል፤ ሕፃናትን አይምሩም፤ ዐይናቸውም ለልጆች አይራራም።
ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
እንግዲህ ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ እሾህንና ኩርንችትን ይበላል፤ ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነዳል፤ ጢሱም ተትጐልጉሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።
ሕዝቡም ሁሉ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” ብለው መለሱ።
ስጡ ይሰጣችኋልም፤ በመልካምም መስፈሪያ የተጠቀጠቀና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና።”
ምሕረት ያላደረገ ሁሉ ያለ ምሕረት ይፈረድበታልና፤ ምሕረትም ፍርድን ያሸንፋል።