Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 109:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ተተኪ አይኑረው፥ በቀጣይ ትውልድ ስማቸው ይደምሰስ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዘሩ ተለይቶ ይጥፋ፤ ስማቸውም በሚቀጥለው ትውልድ ይደምሰስ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለስሙ መጠሪያ የሚሆን አንድ ልጅ እንኳ አይቅርለት፤ ከአንድ ትውልድ በኋላ የሚያስታውሰው አይኑር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 109:13
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፥ የክፉ ስም ግን ይጠፋል።


ጌታ ፍርድን ይወድዳልና፥ ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና፥ ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል፥ የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።


ዘርም ትውልድም በሕዝቡ መካከል አይሆንለትም፥ በመኖሪያውም ውስጥ የሚቀመጥ ሰው አይቀርለትም።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወንለት የለም፥ በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ ከእንግዲህ ወዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።”


በተቈጣህም ጊዜ እንደ እሳት እቶን ታደርጋቸዋለህ፥ ጌታ በቁጣው ይውጣቸዋል፥ እሳትም ትበላቸዋለች።


ልጆቹ አስጸያፊ ነገር ሲያደርጉ እርሱ ባለመከልከሉ፥ ዔሊ በሚያውቀው ኃጢአት ምክንያት በቤተሰቡ ላይ ለዘለዓለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር።


ጌታ በእርሱ ላይ ቁጣውና ቅናቱ ይነድበታል እንጂ ለዚያ ሰው ፈጽሞ ይቅርታ አያደርግም። በዚህ መጽሐፍ የተጻፈው ርግማን ሁሉ ይወርድበታል፤ ጌታ ስሙን ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል።


ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ ባሳረፈህ ጊዜ፥ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ መደምሰስን፥ ይህንን አትርሳ።”


አጠፋቸው ዘንድ፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች እደመስስ ዘንድ ተወኝ፥ አንተንም ከእነርሱ የበረታና የበዛ ሕዝብ አደርግሃለሁ።’


ወንድ ልጅስ ባይኖረው የአባታችን ስም ከወገኑ መካከል ለምን ይጠፋል? በአባታችን ወንድሞች መካከል ርስትን ስጠን።”


ዚምሪ እንደ ነገሠ ወዲያውኑ የባዕሻ ቤተሰብ አባላት የሆኑትን በሙሉ ገደለ፤ የባዕሻ ዘመድና ወዳጅ የሆነውን ወንድ ሁሉ በሞት ቀጣ።


መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፥ በሜዳም ስም አይቀርለትም።


ፍሬአቸውን ከምድር ዘራቸውንም ከሰው ልጆች ታጠፋለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች