ምሳሌ 8:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአፌ ቃላት ሁሉ ጽድቅ ናቸው፥ በውስጣቸውም ምንም ጠማማና ጠመዝማዛ ነገር የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአንደበቴ የሚወጡት ቃሎች ሁሉ ጽድቅ ናቸው፤ አንዳቸውም ጠማማና ግራ የሚያጋቡ አይደሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የምናገረው ሁሉ እውነት ነው፤ ጠማማ ወይም ወልጋዳ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአፌ ቃላት ሁሉ እውነት ናቸው፤ ጠማማና እንቅፋት በውስጣቸው የለም። |
ይህ ከኤዶምያስ፥ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፥ አለባበሱ ያማረ፥ በጉልበቱ ጽናት የሚራመድ ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ።”
በዚህም በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ሆናችሁ በዚህ ዓለም እንደ ከዋክብት የምታበሩ፥ ያለ ነቀፋ የዋሆችና ነውርም የሌለባችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ትሆናላችሁ፤