Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 14:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ፌዘኛ ሰው ጥበብን ይፈልጋል አያገኛትም፥ ለአስተዋይ ግን እውቀትን ማግኘት አያስቸግረውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ፌዘኛ ጥበብን ይሻል፤ ሆኖም አያገኛትም፤ ዕውቀት ግን ለአስተዋዮች በቀላሉ ትገኛለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ፌዘኛ ሰው ጥበብን ይፈልጋል፤ አያገኛትም። አስተዋዮች ግን ዕውቀትን በቀላሉ ይገበያሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በክፉዎች ዘንድ ጥበብን ትፈልጋለህ፥ አታገኛትምም፤ ዕውቀት ግን በብልሆች ዘንድ በቀላሉ ይገኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 14:6
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።


ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው፥ ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤


እነርሱ ለሚያስተውል የቀኑ ናቸው፥ እውቀትንም ላገኟት ትክክል ናቸው።


ጥበበኞች አፍረዋል ደንግጠዋል ተማርከዋልም፤ እነሆ፥ የጌታን ቃል ጥለዋል፤ ምን ዓይነት ጥበብ አላቸው?


ወደ ሕጉና ወደ ምስክር ቃሉ ሂዱ! እነርሱም እንዲህ ያለውን ቃል ባይናገሩ የንጋት ብርሃን አይበራላቸውም።


ለራሱ ጠቢብ የሆነ የሚምስለውን ሰው አየኽውን? ከእርሱ ይልቅ ሞኝ ተስፋ አለው።


ሰነፍ የጥበብን ነገር አይወድድም፥ በልቡ ያለውን ሁሉ መግለጥ ብቻ ይወድዳል እንጂ።


በአስተዋይ ፊት ጥበብ ትኖራለች፥ የሰነፍ ዐይን ግን በምድር ዳርቻ ነው።


ዐይኖቼን ክፈት፥ ከሕግህም ተኣምራትህን አያለሁ።


ጠቢብ እነዚህን በመስማት ዐዋቂነትን ይጨምራል፥ አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል።


የታመነ ምስክር አይዋሽም፥ የሐሰት ምስክር ግን በሐሰት ይናገራል።


ከሰነፍ ሰው ፊት ራቅ፥ በእርሱ ዘንድ የእውቀትን ከንፈር አታገኝምና።


ጥበብ ለሞኝ ሰው ከፍ ብላ የራቀች ናት፥ በከተማውም በር ላይ መናገር አይችልም።


የአፌ ቃላት ሁሉ ጽድቅ ናቸው፥ በውስጣቸውም ምንም ጠማማና ጠመዝማዛ ነገር የለም።


ፌዘኛ ሰው የሚዘልፈውን አይወድድም፥ ወደ ጠቢባንም አይሄድም።


በሰነፍ እጅ የጥበብ መግዣ ገንዘብ መኖሩ ስለ ምንድነው? ጥበብን ይገዛ ዘንድ አእምሮ የለውምና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች