በመኝታዬ ከርቤንና ዓልሙን ቀረፋም ረጭቼበታለሁ።
ዐልጋዬን፣ የከርቤ፣ የአደስና የቀረፋ ሽቱ አርከፍክፌበታለሁ።
ከርቤ አልሙንና ቀረፋ ከተባሉት ቅመሞች የተሠራ ሽቶ አርከፍክፌበታለሁ።
ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ፥ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን ቀባህ።
በልብሶችህ ሁሉ ከርቤና ሽቱ ዝባድም አሉ፥ በዝሆን ጥርስ ከተዋቡ ቤተ መንግሥቶች ይልቅ የበገናና የመሰንቆ ድምጽ ደስ ያሰኙሃል።
“ምርጥ የሆኑትን ቅመሞች ለራስህ ውሰድ፤ ፈሳሽ ከርቤ አምስት መቶ ሰቅል፥ ግማሽ ይኸውም ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል የቀረፋ ቅመም፥ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥
ና፥ እስኪ ነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ፥ በተወደደ መተቃቀፍም ደስ ይበለን።
መዓዛም እንደ ከርቤና እንደ ዕጣን የሆነችው፥ ከልዩ ከነጋዴ ቅመም ሁሉ የሆነችው፥ ይህች ከምድረበዳ እንደ ጢስ ምስሶ የወጣችው ማን ናት?
ከኡዛል ቭዳንና ያቫን ዕቃዎችሽን ይለውጡ ነበር፤ የተሠራ ብረትና ብርጉድ ቀረፋም ሸቀጥሽ ነበረ።
እንዲሁም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ።