Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 30:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 “ምርጥ የሆኑትን ቅመሞች ለራስህ ውሰድ፤ ፈሳሽ ከርቤ አምስት መቶ ሰቅል፥ ግማሽ ይኸውም ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል የቀረፋ ቅመም፥ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “ምርጥ ቅመሞችን፣ ዐምስት መቶ ሰቅል ፈሳሽ ከርቤ፣ ግማሽ ይኸውም ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ጣፋጭ ቀረፋ፣ ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ከሙን፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ምርጥ የሆኑ ቅመሞችን፥ ስድስት ኪሎ ግራም ፈሳሽ ከርቤ፥ ሦስት ኪሎ ግራም ጣፋጭ ሽታ ያለውን ቀረፋ፥ ሦስት ኪሎ ግራም ጣፋጭ ሽታ ያለውን የጠጅ ሣርና፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 “አን​ተም ክቡ​ሩን ሽቱ ውሰድ፤ የተ​መ​ረጠ የከ​ርቤ አበባ አም​ስት መቶ ሰቅል፥ የዚ​ህም ግማሽ ጣፋጭ ቀረፋ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤ ያማረ የጠጅ ሣርም እን​ዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አንተም ክቡሩን ሽቱ ውሰድ፤ የተመረጠ ከርቤ አምስት መቶ ሰቅል፥ ግማሽም ጣፋጭ ቀረፋ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 30:23
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከኡዛል ቭዳንና ያቫን ዕቃዎችሽን ይለውጡ ነበር፤ የተሠራ ብረትና ብርጉድ ቀረፋም ሸቀጥሽ ነበረ።


ናርዶስ ከቀጋ ጋር፥ የሽቱ ሣርና ቀረፋ፥ ከልዩ ልዩ የዕጣን ዕፀዋት ጋር፥ ከርቤና እሬት ከምርጥ ቅመሞች ሁሉ ጋር።


የሳባና የራዕማ ነጋዴዎች እነዚህ ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ምርጥ በሆኑ ቅመማ ቅመሞች ሁሉ፥ በክበረ ድንጋይ ሁሉና በወርቅ ሸቀጥሽን ይለውጡ ነበር።


ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣንን፥ ከሩቅም አገር የከበረውንም ዘይት ታመጡልኛላችሁ? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አልቀበለውም፥ ሌላ መሥዋዕታችሁም ደስ አያሰኘኝም።


ውዴ ለእኔ በጡቶቼ መካከል እንደሚያርፍ እንደ ተቋጠረ ከርቤ ነው።


ዘይትህ መልካም መዓዛ አለው፥ ስምህ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፥ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ።


በመኝታዬ ከርቤንና ዓልሙን ቀረፋም ረጭቼበታለሁ።


ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ፥ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን ቀባህ።


የተቀደሰ የቅባት ዘይት፥ ንጹሕና መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን ቀማሚ እንደሚሠራው አደረገ።


ለመብራት የሚሆን ዘይት፥ ለቅባት የሚሆን ዘይትና ለጣፋጭ ዕጣን የሚሆን ቅመም፥


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦


ብርጉድ አምስት መቶ ሰቅል በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት፥ አንድ የኢን መሥፈሪያ የወይራ ዘይት፥


የቅባቱን ዘይት፥ ለመቅደሱ የሚሆን መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን እንዳዘዝሁህ ሁሉ እንዲሁ ያድርጉ።”


ቅመማቅመም፥ ለመብራት የሚሆን ዘይት፥ ለቅባት የሚሆን ዘይት፥ ለጣፋጭ ሽታ ዕጣንን አመጡ።


ከዚያም ሳሙኤል የዘይቱን ብርሌ ወስዶ፥ ዘይቱን በሳኦል ራስ ላይ ካፈሰሰ በኋላ ሳመው፥ እንዲህም አለው፤ “በርስቱ ላይ ገዥ ትሆን ዘንድ ጌታ ቀብቶህ የለምን?


ካህኑም ሳዶቅ ከድንኳኑ የቅባቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባ፥ ቀንደ መለከትም ነፉ፥ ሕዝቡም ሁሉ፦ “ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ!” አሉ።


ከካህናቱም ልጆች አንዳንዶቹ የሽቶውን ቅባት ይቀምሙ ነበር።


ዕጣንም በገንዘብ አልገዛህልኝም፤ በመሥዋዕትህም ስብ አላጠገብኸኝም፤ ነገር ግን በኃጢአትህ አስቸገርከኝ፥ በበደልህም አደከምከኝ።


“የካህኑም የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት መዓዛውም በሚያምር ዕጣን ላይ፥ ሁልጊዜም በሚቀርበው በእህሉ ቁርባንና በቅባቱ ዘይት ላይ ይሾም፤ ማደሪያውን ሁሉ፥ በእርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ መቅደሱንና ዕቃውን ይቆጣጠር።”


ከእነርሱም አንዳንዶቹ በመቅደሱ ዕቃ ሁሉ በመልካሙም ዱቄት፥ በወይን ጠጁም፥ በዘይቱም፥ በዕጣኑም፥ በሽቶውም ላይ ሹሞች ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች