ዘኍል 24:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከያዕቆብም የሚወጣ ገዥ ይሆናል፥ ከከተማውም በሕይወት የተረፉትን ያጠፋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገዥ ከያዕቆብ ይወጣል፤ የተረፉትንም የከተማዪቱን ነዋሪዎች ይደመስሳል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከያዕቆብ አንድ ገዢ ይወጣል፤ በከተማም ውስጥ የተረፉትን ጠራርጎ ያጠፋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከያዕቆብም ኀያል ሰው ይወጣል፤ ከከተማውም የቀሩትን ያጠፋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከያዕቆብም የሚወጣ ገዥ ይሆናል፥ ከከተማውም የቀሩትን ያጠፋል። |
በለዓምም አማሌቅን አይቶ ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “የአሕዛብ መጀመሪያ የሆነ አማሌቅ ነበረ፤ ፍጻሜው ግን ወደ ጥፋት የሚያመራ ይሆናል።”