ስለዚህም ዳዊት ጌታን፥ “ፍልስጥኤማውያንን ወጥቼ ልውጋቸው? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጠኛለህ?” ሲል ጠየቀ። ጌታም፥ “ሂድ፤ በእርግጥ ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ” አለው።
ዘኍል 21:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እርሱንና ሕዝቡን ሁሉ ምድሪቱንም አሳልፌ በእጅህ ሰጥቼአለሁና አትፍራው፤ በሐሴቦንም በተቀመጠው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግኸው እንዲሁ ታደርግበታለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እርሱን ከመላው ሰራዊቱና ከምድሩ ጋራ በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁና አትፍራው። በሐሴቦን ሆኖ ይገዛ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ላይ ያደረግህበትን ሁሉ በርሱም ላይ አድርግበት” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሰው አትፍራው፤ በእርሱና በሕዝቡ በምድሪቱም ላይ ድል እንድትጐናጸፍ አደርግሃለሁ፤ በሐሴቦን ሆኖ ይገዛ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ ያደረግኸውን ሁሉ በዚህም ላይ አድርግበት።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “እርሱንና ሕዝቡን ሁሉ፥ ምድሪቱንም አሳልፌ በእጅህ ሰጥቼሃለሁና አትፍራው፤ በሐሴቦንም በተቀመጠው በአሞሬዎን ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግህ እንዲሁ ታደርግበታለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እርሱንና ሕዝቡን ሁሉ ምድሪቱንም አሳልፌ በእጅህ ሰጥቼአለሁና አትፍራው፤ በሐሴቦንም በተቀመጠው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግህ እንዲሁ ታደርግበታለህ አለው። |
ስለዚህም ዳዊት ጌታን፥ “ፍልስጥኤማውያንን ወጥቼ ልውጋቸው? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጠኛለህ?” ሲል ጠየቀ። ጌታም፥ “ሂድ፤ በእርግጥ ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ” አለው።
በዚህን ጊዜ አንድ ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “ጌታ ‘ከቤንሀዳድ ሠራዊት ብዛት የተነሣ አትፍራ! እኔ ዛሬ በዚህ ሠራዊት ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አደርጋለሁ፤ አንተም ደግሞ እኔ ጌታ መሆኔን ታውቃለህ’ ይልሃል” አለው።
አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “ጌታ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘ሶርያውያን ጌታ የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም’ ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ በሆነው ሠራዊታቸው ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ አንተና ሕዝብህም እኔ ጌታ መሆኔን ታውቃላችሁ” አለው።
ብቻ፥ በጌታ ላይ አታምፁ፤ ለእኛ እንደ እንጀራ ቁራሽ ናቸውና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ ጌታም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው።”
“የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፥ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ መንፈሱን አደንድኖታልና ልቡንም አጽንቶታልና።”
እንዲህም ይበል፦ ‘እስራኤል ሆይ ስማ፤ በዛሬው ቀን ጠላቶቻችሁን ለመግጠም ወደ ጦርነት ልትገቡ ነው፤ ልባችሁ አይባባ፤ አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ በጠላቶቻችሁ ፊት አትሸበሩ፤
ከራፋያውያን ወገን የባሳን ንጉሥ ዖግ ብቻውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አልጋው የብረት አልጋ ነበረ፥ እርሱ በአሞን ልጆች አገር በራባት አለ፥ ቁመቱ ዘጠኝ ክንድ የጎኑም ስፋት አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።
ነገሥታቶቻቸውንም በእጅህ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች ታጠፋለህ፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ማንም ተቋቁሞህ በፊት ሊቆም አይችልም።