ነህምያ 11:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሕዝቡ መሪዎች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀረው ሕዝብ ከአሥሩ አንዱ እጅ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ የቀሩት ዘጠኙ ደግሞ በሌሎች ከተሞች እንዲቀመጡ ዕጣ ተጣጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የሕዝቡ መሪዎች መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከቀረው ሕዝብ ከዐሥር አንዱ እጅ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፣ የቀሩት ዘጠኙ እጅ ደግሞ በየራሳቸው ከተሞች እንዲኖሩ ዕጣ ተጣጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሪዎቹ መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከሌላውም ሕዝብ መካከል ከየዐሥር ቤተሰብ አንዱ እጅ ቅድስት በሆነችው በኢየሩሳሌም ከተማ እንዲኖር በዕጣ ተመረጠ፤ የቀሩት ሰዎች ግን በሌሎች መንደሮችና ከተሞች ሁሉ ኑሮአቸውን መሠረቱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሕዝቡም አለቆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀሩትም ሕዝብ ከዐሥሩ ክፍል አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ ዘጠኙም በሌሎች ከተሞች ይቀመጡ ዘንድ ዕጣ ተጣጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሕዝቡም አለቆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፥ ከቀሩትም ሕዝብ ከአሥሩ ክፍል አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ ዘጠኙም በሌሎች ከተሞች ይቀመጡ ዘንድ ዕጣ ተጣጣሉ። |
እኛም፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ እንጨት ቁርባን ዕጣ ተጣጣልን፥
ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።
ሲጸልዩም “የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ! ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ይሄድ ዘንድ በተዋት በዚህች አገልግሎትና ሐዋርያነት ስፍራን እንዲቀበል የመረጥኸውን ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን ሹመው፤” አሉ።