እንደገናም ሄዶ መጀመሪያ የጸለየውን ደግሞ ጸለየው።
እንደ ገናም ሄዶ መጀመሪያ የጸለየውን ደግሞ ጸለየ።
እንደገናም ሄዶ፥ ያንኑ የፊተኛውን ቃል በመናገር ጸለየ።
ደግሞም ሄዶ ያንኑ ቃል ጸለየ።
“ስትጸልዩ እንደ አሕዛብ የሚደጋገሙ ቃላትን አትጠቀሙ፥ እነርሱ ብዙ በመናገራቸው የሚሰሙ ይመስላቸዋልና።
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ፤ ጸልዩም፤ መንፈስ ዝግጁ ነው፥ ሥጋ ግን ደካማ ነው።”
ዳግመኛም ሲመለስ ዐይናቸውን እንቅልፍ ከብዶት ተኝተው አገኛቸው፤ የሚመልሱለትንም አያውቁም ነበር።
ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንደሚገባቸው የሚያስተምር ምሳሌን ነገራቸው፤
ይህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።
እርሱም ሥጋ ለብሶ በምድር በሚመላለስ ጊዜ፥ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል፥ ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ስለ ጻድቅ ፍርሃቱም ጸሎቱ ተሰማለት፤