አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይም አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምንጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም!” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።
ሉቃስ 11:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሕግ አዋቂዎችም አንዱ መልሶ፦ “መምህር ሆይ! ይህን ስትል እኮ እኛን ደግሞ መስደብህ ነው፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕግ ዐዋቂዎች አንዱ መልሶ “መምህር ሆይ፤ እንዲህ ስትናገር እኮ እኛንም መስደብህ ነው” ሲል መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሕግ መምህራኑም አንዱ ኢየሱስን፥ “መምህር ሆይ፥ ይህንን ስትል እኛንም መስደብህ ነው!” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሕግ ዐዋቂዎችም አንዱ መልሶ፥ “መምህር ሆይ፥ ይህን ስትል እኛን እኮ መስደብህ ነው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሕግ አዋቂዎችም አንዱ መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ ይህን ማለትህ እኛን ደግሞ መስደብህ ነው አለው። |
አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይም አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምንጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም!” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።
እንዲሰሙኝስ ለማን እናገራለሁ? ለማንስ አስጠነቅቃለሁ? እነሆ፥ ጆሮአቸው ያልተገረዘ ነው፥ መስማትም አይችሉም፤ እነሆ፥ የጌታ ቃል ለስድብ ሆኖባቸዋል፥ ደስም አያሰኛቸውም።
እርሱም እንዲህ አለ፦ እናንተ ሕግ አዋቂዎች ደግሞ ወዮላችሁ! ለመሸከም ከባድ የሆነውን ሸክም ሰዎችን ታሸክማላችሁ፥ ራሳችሁ ግን በአንዲት ጣታችሁ እንኳ ሸክሙን አትነኩትምና።