ዮሐንስ 12:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፋሲካም በፊት በስድስተኛው ቀን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፋሲካ በዓል ስድስት ቀን ሲቀረው፣ ኢየሱስ ከሞት ያስነሣው አልዓዛር ወደሚኖርበት፣ ወደ ቢታንያ መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአይሁድ የፋሲካ በዓል ሊከበር ስድስት ቀን ሲቀረው፥ ኢየሱስ ወደ ቢታንያ ሄደ፤ ቢታንያ ኢየሱስ ከሞት ያስነሣው አልዓዛር የሚኖርባት መንደር ነች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፋሲካም በፊት በስድስተኛው ቀን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ። |
ኢየሱስም ኢየሩሳሌም ደረሰ፤ ከዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ ተመለከተ፤ ቀኑም ስለመሸ ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ።
እነሆም፥ በዚያች ከተማ ኀጢአተኛ የነበረች አንዲት ሴት፥ በፈሪሳዊው ቤት በማዕድ እንደተቀመጠ ባወቀች ጊዜ፥ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ አምጥታ ነበር።
ሞቶ የነበረውም ሰው እጆቹና እግሮቹ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፈቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ፤ ተዉት፤” አላቸው።
ከአይሁድም ብዙ ሰዎች በዚያ እንደ ነበረ አውቀው መጡ፤ የመጡትም በኢየሱስ ምክንያት ብቻ ሳይሆን ከሙታን ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር።