Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 11:55 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

55 የአይሁድም ፋሲካ ቀርቦ ነበር። ብዙ ሰዎችም ራሳቸውን ያነጹ ዘንድ ከፋሲካ በፊት ከአገሩ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

55 የአይሁድ ፋሲካ እንደ ተቃረበም፣ በዓሉ ከመድረሱ በፊት የመንጻት ሥርዐት ለማድረግ ብዙዎች ከአገር ቤት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

55 የአይሁድ የፋሲካ በዓል ቀርቦ ነበር፤ ብዙዎቹም የፋሲካ በዓል ከመድረሱ በፊት፥ ራሳቸውን ለማንጻት ከየቦታው ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

55 የአ​ይ​ሁ​ድም የፋ​ሲካ በዓል ቀርቦ ነበር፤ ብዙ ሰዎ​ችም ከበ​ዓሉ አስ​ቀ​ድሞ ራሳ​ቸ​ውን ያነጹ ዘንድ ከየ​ሀ​ገሩ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጥ​ተው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

55 የአይሁድም ፋሲካ ቀርቦ ነበር። ብዙ ሰዎችም ራሳቸውን ያነጹ ዘንድ ከፋሲካ በፊት ከአገሩ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 11:55
30 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከፋሲካም በፊት በስድስተኛው ቀን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ።


የአይሁድ በዓል ፋሲካም ቀርቦ ነበር።


የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።


ጌታም ሙሴን አለው፦ “ወደ ሕዝቡ ሂድ፥ ዛሬና ነገን ቀድሳቸው፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፤


ስለዚህ ያዕቆብ ለቤተሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፦ “እንግዶቹን አማልክት ከመካከላችሁ አስወግዱ ንጹሐንም ሁኑ፥ ልብሳችሁንም ለውጡ፥


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች! እጃችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።


ሰው ግን ራሱን ይመርምር፤ እንዲሁም ከኅብስቱ ይብላ፤ ከጽዋውም ይጠጣ፤


ይህንም ሳደርግ ሳለሁ ሕዝብ ሳይሰበሰብ ሁከትም ሳይሆን በመቅደስ ስነጻ አገኙኝ።


ኢየሱስንም ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱት፤ ማለዳም ነበረ፤ እነርሱም እንዳይረክሱ፥ ይልቁንም የፋሲካን በግ እንዲበሉ በማለት ወደ ገዢው ግቢ አልገቡም።


ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን፥ የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው።


ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።


አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።


የፋሲካና የቂጣ በዓል ሊከበር ሁለት ቀን ሲቀረው፥ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ኢየሱስን የሚይዙበትና የሚገድሉበትን ዘዴ ይፈልጉ ነበር።


እንዲህም ሆነ፤ ኢየሱስ እነዚህን ቃሎች ሁሉ ተናግሮ ከፈጸመ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦


እጆቼን በንጽሕና አጥባለሁ፥ አቤቱ፥ መሠዊያህን እዞራለሁ፥


የግብዣውም ቀኖች ባለፉ ጊዜ ኢዮብ፦ “ምናልባት ልጆቼ በድለው፥ እግዚአብሔርንም በልባቸው ሰድበው ይሆናል” ብሎ ይልክና ይቀድሳቸው ነበር፥ ኢዮብም ማልዶ ይነሣና እንደ ቁጥራቸውም ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርብ ነበር። ኢዮብም ሁልጊዜ እንዲህ ያደርግ ነበር።


ሳሙኤልም፥ “አዎን፤ ለሰላም ነው፤ የመጣሁትም ለጌታ መሥዋዕት ላቀርብ ነው፤ እናንተም ራሳችሁን ቀድሳችሁ ከእኔ ጋር ወደ መሥዋዕቱ ኑ” ሲል መለሰላቸው። ከዚያም እሴይንና ልጆቹን ቀደሳቸው፤ ወደ መሥዋዕቱም እንዲመጡ ጠራቸው።


የሞተ ሰው ሬሳን በመንካት የረከሱ ሰዎችም ነበሩ፥ ስለዚህም በዚያ ቀን የፋሲካን በዓል ለማክበር አልቻሉም ነበር። በዚያም ቀን በሙሴና በአሮን ፊት ቀረቡ።


“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ከእናንተ ወይም ከትውልዶቻችሁ ዘንድ ሰው ሬሳን በመንካት ቢረክስ፥ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ፥ እርሱ እንዲህም ሆኖ እንኳ ለጌታ የፋሲካን በዓል ያክብር።


“ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንደሚሆን ታውቃላችሁ፤ የሰው ልጅም ሊሰቀል ተላልፎ ይሰጣል።”


ፋሲካም ተብሎ የሚጠራው የቂጣ በዓል ቀረበ።


እነዚህንም ይዘህ ከእነርሱ ጋር ንጻ፤ ራሳቸውንም እንዲላጩ ገንዘብ ክፈልላቸው፤ ሁሉም ስለ አንተ የተማሩት ከንቱ እንደ ሆነና አንተ ራስህ ደግሞ ሕጉን እየጠበቅህ በሥርዓት እንድትመላለስ ያውቃሉ።


በዚያን ጊዜ ጳውሎስ ሰዎችን ይዞ በማግሥቱ ከእነርሱ ጋር እየነጻ፥ መንጻታቸውን የሚፈጽሙበትን ቀን አስታውቆ ወደ መቅደስ ገባ። በዚያም ቀን ስለ እያንዳንዳቸው መሥዋዕትን አቀረቡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች