ሞዓብ ጠፍታለች፥ ልጆችዋም ጩኸትን አሰምተዋል።
ሞዓብ ትሰበራለች፤ ልጆቿም ጩኸት ያሰማሉ።
“ሞአብ ተደምስሳለች፤ ልጆችዋም ጩኸትን ያሰማሉ።
ሞአብ ጠፍታለች፤ ይህንም በሴጎር ተናገሩ።
ሕፃኖችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው።
ያም ሰው ጌታ ሳይጸጸት እንደ ገለበጣቸው ከተሞች ይሁን፥ በማለዳም ልቅሶን በቀትርም ጩኸትን ይስማ፤
መፍረስና ታላቅ ጥፋት፥ የሚል የጩኸት ድምፅ ከሖሮናይም ተሰማ።
በሉሒት አቀበት መራር ልቅሶ እያለቀሱ ይወጣሉና፥ በሖሮናይምም ቁልቁለት የጥፋትንና የጣርን ጩኸት ሰምተዋል።