ዘፍጥረት 48:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም ለአባቱ፦ “እግዚአብሔር በዚህ የሰጠኝ ልጆቼ ናቸው” አለ። እርሱም፦ “እባርካቸው ዘንድ ወደዚህ አቅርብልኝ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍም፣ “እነዚህ እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ብሎ ለአባቱ መለሰለት። እስራኤልም፣ “አቅርባቸውና ልመርቃቸው” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍም “እነዚህ እግዚአብሔር በዚህ አገር ሳለሁ የሰጠኝ የእኔ ልጆች ናቸው” ብሎ ለአባቱ መለሰለት። ያዕቆብም “እባርካቸው ዘንድ ወደ እኔ አቅርብልኝ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም ለአባቱ ፥ “እግዚአብሔር በዚህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለው። ያዕቆብም፥ “እባርካቸው ዘንድ ወደ እኔ አቅርብልኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ለአባቱ፦ እግዚአብሔር በዚህ የሰጠኝ ልጆቼ ናቸው አለ። እርሱም፦ እባርካቸው ዘንድ ወደዚህ አቅርብልኝ አለ። |
ዓይኑን አንስቶም ሴቶችንና ልጆችን ባየ ጊዜ፥ “እነዚህ ምኖችህ ናቸው?” አለ። እርሱም፦ “እግዚአብሔር ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለ።
እነዚህም ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው፥ አባታቸው የነገራቸው ይህ ነው፥ ባረካቸውም፥ እያንዳንዳቸውን እንደ በረከታቸው ባረካቸው።
እነዚህ ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ እንዲያደርጉ በእግዚአብሔር ቃል የንጉሡ ባለ ራእይ የሆነው የኤማን ልጆች ነበሩ። እግዚአብሔርም ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶች ልጆችንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ሰጠው።