ዘፍጥረት 4:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ለእርሱ፥ “እንዲህስ አይሆንም! ማንም ቃየንን የሚገድል፥ ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት ይደርስበታል” አለው። ጌታም ቃየንን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን፣ “የለም! እንደርሱ አይሆንም፤ ማንም ቃየንን ቢገድል፣ ሰባት ዕጥፍ የበቀል ቅጣት ይቀበላል” አለው፤ ስለዚህ፣ ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው እግዚአብሔር በቃየን ላይ ምልክት አደረገለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ግን “ማንም አይነካህም፤ አንተን የሚገድል ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት ይደርስበታል” አለው። ስለዚህ እግዚአብሔር ቃየልን ማንም ቢያገኘው እንዳይገድለው የሚያስጠነቅቅ ልዩ ምልክት አደረገለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አለው፥ “እንዲህ አይደለም፤ እንግዲህ ቃየልን የገደለ ሁሉ ሰባት እጥፍ ይበቀልበታል።” እግዚአብሔርም ቃየልን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እርሱን አለው፤ እንግዲህ ቃየንን የገደለ ሁሉ ሰባት እጥፍ ይበቀልብታል። እግዚአብሔርም ቃየንን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት። ፕ |
ጌታ በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባዕሻና በቤተሰቡ ላይ ያን የትንቢት ቃል የተናገረበት ምክንያት፥ ባዕሻ በፈጸመው ኃጢአት ጌታን ስላሳዘነ ነበር፤ ባዕሻ ጌታን ያስቆጣውም ከእርሱ ፊት የነበረው ንጉሥ ባደረገው ዓይነት ስለ ሠራው ክፉ ነገር ብቻ ሳይሆን የኢዮርብዓምንም ቤተሰብ ሁሉ በመግደሉ ጭምር ነው።
ጌታም እንዲህ አለው፦ በከተማይቱ መካከል፥ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኩሰት ሁሉ በሚተክዙና በሚያለቅሱ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክትን አድርግ።
ሽማግሌ፥ ወጣት፥ ድንግል፥ ሕፃናትንና ሴቶችን ግደሉ፥ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፥ በመቅደሴም ጀምሩ። በቤቱ ፊት ለፊት ከነበሩት ሽማግሌዎች ጀመሩ።
ጌታም እንዲህ አለው፦ “ከጥቂት ዘመን በኋላ የኢይዝራኤልን ደም በኢዩ ቤት ላይ እበቀላለሁና፥ ከእስራኤልም ቤት መንግሥትን እሽራለሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው፤
የሥቃያቸውም ጢስ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ እንዲሁም የስሙን ምልክት የሚቀበሉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”
ሌላም ሦስተኛ መልአክ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ ተከተላቸው፤ “ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግድ በግምባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር፥