ዘፍጥረት 27:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም አባቱን አለው፦ “የበኩር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ፥ እንዳዘዝኸኝ አደረግሁ፥ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና በልና ተቀመጥ፥ ካደንሁትም ብላ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም አባቱን፣ “እኔ የበኵር ልጅህ ዔሳው ነኝ፤ ያዘዝኸኝን አድርጌአለሁ፤ እስኪ ቀና በልና እንድትመርቀኝ ዐድኜ ካመጣሁት ብላ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም “የበኲር ልጅህ ዔሳው ነኝ፤ እነሆ፥ እንዳዘዝከኝ አድርጌአለሁ፤ እንድትመርቀኝ እስቲ ቀና በልና ያመጣሁልህን የአደን ሥጋ ተመገብ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም አባቱን አለው፥ “የበኵር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ፤ እንዳዘዝኸኝ አደረግሁ፤ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና ብለህ ተቀመጥ፤ ካደንሁትም ብላ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም አባቱን አለው፦ የበኵር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ እንዳዘዝኽኝ አደረግሁ፤ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና በልና ተቀመጥ ካደንሁትም ብላ። |
የወንድምህ ቁጣ ከአንተ እስኪመለስ ድረስ፥ ያደረግህበትንም እስኪረሳው ድረስ፥ ከዚያም ልኬ አስመጣሃለሁ፥ በአንድ ቀን ሁለታችሁን ለምን አጣለሁ?”
ከዚህ በኋላ ከቤትኤል የመጣው ሽማግሌ ነቢይ “እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከጌታ የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል” አለው፤ ነገር ግን ዋሽቶ ነበር።
ስለዚህ ኢዮርብዓም ሚስቱን እንዲህ አላት፦ “የእኔ ሚስት መሆንሽን ማንም እንዳያውቅ ልብስሽን ለውጠሽ ሌላ ሴት በመምሰል እኔ የእስራኤል ንጉሥ እንደምሆን የትንቢት ቃል የተናገረው ነቢዩ አኪያ ወደሚኖርባት ወደ ሴሎ ሂጂ።፤
እናንተም፦ “ከሞት ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፥ ከሲኦልም ጋር ተማምለናል፤ ሐሰትን መሸሸጊያችን አድርገናልና፥ በሐሰትም ተሰውረናልና የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም” ስላላችሁ፥